ዓለማችን እያደር ዲጂታል እየሆነች የመምጣትዋ ነገር ኢንዱስትሪዎች ከጥሬ ገንዘብ ቅብብሎሽ ነፃ ወደ ሆነ የክፍያ ሥርዓት እንዲሸጋገሩ ግድ ብሏል፡፡ በዲጂታል የክፍያ ስልቶች ደንበኞች ያለ ጥሬ ገንዘብ የነዳጅ ግዢ መፈፀም ከማስቻሉም በላይ ጊዜን በመቆጠብ መጭበርበርንም ያስወግዳል፡፡
ኮፔይ ኢ-ብር በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ የቀረበና ደንበኞች የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም ለነዳጅ ግዢ ክፍያ የሚፈፅሙበት ዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ነው፡፡
ደንበኞች ኮፔይ ኢ-ብርን ለመጠቀማቸው በርካታ ምክንያቶች ሲኖሯቸው ዋና ዋናዎቹ፡-
ቀላል – አጠቃቀሙ በጣም ቀላል ሲሆን ደንበኞች ከሂሳባቸው ጋር በማገናኘት ክፍያውን በቀላሉ ለመፈፀም የሚያስችል ነው፡፡
ፈጣን– ኮፔይ ኢ-ብር ጊዜ ቆጣቢ ደንበኞች ወዲያውኑ ወይም በጥቂት ሰከንዶች ውስጥ ክፍያ መፈፀም እንዲችሉ የሚያደርግ ነው፡፡
ተስማሚ– ኮፔይ ኢ-ብር ደንበኞች የባንክ ሂሳብና የዋሌት ሂሳባቸውን ሁለቱንም በአንድ የሞባይል መተግበሪያ መጠቀም የሚችሉበትና ምቾት ያለው ነው፡፡
ደህንነት– እንዳጠቃላይ ደህንነቱ የተጠበቀ ሲሆን ለደንበኞች የፋይናንስ መረጃዎች ጥበቃ የሚደረግበት ነው፡፡
ኮፔይ ኢ-ብርን በመጠቀም ነዳጅ ለመሙላት፡-
- የኮፔይ ኢ-ብርን መተግበሪያ ከአፕስቶር ወይም ጎግል ፕሌይ በማውረድ በሞባይልዎ ይጫኑ
- የኮፔይ ኢ-ብር ሂሳብ ለመክፈት በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የኦኅሥባ ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም 841 በመደወል በራስዎ ይመዝገቡ
- ነዳጅ ማደያ ሲደርሱ በኮፔይ ኢ-ብር እንደሚከፍሉ ለነዳጅ ማደያ ባለሙያ ያሳውቁ
- ክፍያ በነዳጅ ማደያ ባለሙያ ተዘጋጅቶ ይቀርባል
- የክፍያ መጠኑን በማረጋገጥ የምስጢር ቁጥርዎን በማስገባት ክፍያ ይፈፅሙ
በሀገሪቱ ከሚንቀሳቀሱና በላቀ ደረጃ ላይ ከሚገኙ የግል ባንኮች አንዱ በሆነው የኦኅሥባየቀረበውን ኮፔይ ኢ-ብር መተግበሪያ በመጠቀም የነዳጅ ሂሳብዎን በቅፅበት ይክፈሉ።
ይፍጠኑ የነዳጅ ሙሌት ውጣ ውረድን በማስወገድ ኑሮን ያቅሉ!
ነዳጅ መሙላትስ በኮፔይ ኢ-ብር!