ምቹ፡ የኢትዮጵያ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በዲጂታል ብድር ማብቃት።

የንግድ ፍላጎቶችዎን ወደሚረዳ እና እድገትዎን ወደሚደግፍ ወደ ምቹ ዲጂታል ብድር እንኳን በደህና መጡ! አነስተኛ የንግድ ሥራ ካለዎት፤ የተቋቋመ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከሆኑ ውይም ከፍተኛ ተነሳሽነት ያለው ሥራ ፈጣሪ ከሆኑ፣ እንዲያድጉ የሚረዳዎት ምቹ ዲጂታል ብድር አለልዎ።
ስለ ብድር ውጣውረድ፣ ስለማስያዣ ጥያቄ እና ለብድር ጥያቄ ማረጋገጫ ቆይታ፣ ቻው ይበሉ። የፋይናንስ ጉዳዮችዎ፣ ጥቂት ሂደቶች ብቻ!

መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ

Michu login Page image

ለንግድ ሥራዎ የተመቻቸ ብድር

በምቹ ብድር፣ የፋይናንስ ድጋፍ ለሁሉም አካል ተደራሽ እንዲሆን እናምናለን። ለዚህም ነው የሀገራችንን የንግድ ድርጅቶች ፍላጎት መሰረት በማድረግ ሶስት አይነት የብድር ምርቶችን ያዘጋጀነው።

Michu Wabii loan – credit score-based MSME financing

ይህ ብድር፣ የተሻለ የካፒታል መጠን ለሚያስፈልጋቸው መካከለኛ ድርጅቶች የተዘጋጀ ነው። የዋቢ ምቹ ብድር፣ ለንግድ ሥራ ማስፋፊያ፣ ለእቃዎች ግዢ ወይም ለንግድ ስራ እድገት ከብር 50,000 እስከ ብር 100,000 የሚደርስ ብድር ይሰጣል።

Michu Guyyaa loan – short-term digital loan for MSMEs

ለአነስተኛ ንግዶች እና በጎዳና ላይ እየተንቀሳቀሱ ለሚሰሩ ከብር 5,000 እስከ 15,000 ብድር ይሰጣል። የንግድ ፈቃድ የለዎትም? ችግር የለውም! እኛ የምናምነው በችሎታዎ እንጂ በወረቀት ሥራ አይደለም።

Michu Kiyya – 14-day digital loan for small businesses

ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማብቃት የተነደፈ ሆኖ፣ እስከ ብር 30,000 የሚደርሱ ብድሮችን በዝቅተኛ የአገልግሎት ክፍያ እና ቀላል ሂደት ይሰጣል። ይህም፣ በማኅበረሰባቸው ውስጥ ጠንክራው የምሰሩ እና ለውጥ እያመጡ ያሉ ሴቶችን የምንደግፍበት መንገድ ነው።

እንዴት መጠቀም እንደሚቻል

ምቹ፣ ሙሉ ለሙሉ ዲጂታል መሆኑ፣ የሚፈልጉትን ገንዘብ ለማግኘት በጣም ቀላል እና የበለጠ ምቹ ያደርገዋል።
እንዴት እንደሚጠቀሙበት እነሆ፡-

የምቹ መተግበሪያን ያውርዱ

መተግበሪያችን በታዋቂ ፕላትፎርሞች ላይ የሚገኝ ስለሆነ፣ የሚፈልጉትን ፋይናንስ በቀላሉ ማግኘት የሚችሉበት መንገድ ነው።

ይመዝገቡ

መገለጫዎን ይፍጠሩ፤ ከባንክ ሂሳብ ቁጥርዎ ጋር ያገናኙ፤ ስለ ንግድዎ አንዳንድ መሰረታዊ መረጃዎችን ያስገቡ።

Michu login Page image

ብድርዎን ይውሰዱ

ለሚፈልጉት ገንዘብ ሲያመለክቱ፣ ወዲያውኑ ይጸድቃል። የጠየቁት ገንዘብም፣ በቀጥታ ወደ የባንክ ሂሳብ ቁጥርዎ ገቢ ይደረጋል፤ እናም ለመጠቀም ዝግጁ ይሁኑ!

የበለጠ ያስፈጽሙ

ብድርዎን በሰዓቱ ሲመልሱ፣ በ AI-የተደገፈው የምቹ ሥርዓት መበደር የሚችሉትን መጠን ከፍ ያደርገዋል፤ በዚህም ንግድዎ በየደረጃ እንዲያድግ ያግዛል።

ሕይወትን መለወጥ፣ አንድ በአንድ

ምቹ፣ ከ1.47ሚሊዮን በላይ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በመደገፍ፣ በመላ ኢትዮጵያ ተጨባጭ ለውጦችን እያመጣ ይገኛል።

“በገንዘብ እጦት ንግዴ ሲዳከም፣ ምቹ፣ የቤት ኪራይ ሸፍኖልኝ፣ የሱቄ በሮች ክፍት እንዲሆንልኝ ረድቶኛል።

“ምስጋና ለምቹ! ስለ ብድር ማስያዣዎች ሳልጨነቅ፣  ሥራዬን አስፋፍቻለሁ።

“በቢዝነስ ውስጥ ያለች ሴት እንደመሆኔ መጠን የምቹ የአገልግሎት ክፍያን አነስተኛ እና ሂደቱም ህይወትን ቀላል ለማድረግ የሚያስችል ቀላል ጨወታ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።”

የተናገረውን ለመፈጸም የጀገነ

ምቹ፣ በሁሉም የቁጥጥር ማዕቀፎች ውስጥ ጠንክረው የሚሰራ ሲሆን፣ ለደንበኞቻችንም፣ አስተማማኝ እና ምቹ የሆነ የብድር ልምድን ያረጋግጣል።

ተጨማሪ መረጃ

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

አይ፣ የምቹ ዋቢ ብድር እንዲሁ የንግድ ፍቃድ ለሌላቸው የተነደፈ በመሆኑ የንግድ ፈቃድ አያስፈልግም።

እንደተጠየቀ ወዲያውኑ በቀጥታ ወደ የባንክ ሂሳብ ቁጥርዎ ገቢ ይደረጋል።

ብድርዎን በወቅቱ ከመለሱ፣ ለወደፊት የብድር ጥያቄዎት ሊበደሩ የሚችሉት የገንዘብ መጠን ይጨምራል፤ ለ AI ስርዓት ምስጋና ይግባውና ይህንን በራሱ ያስተካከላል።

ንግድዎ ማደግ ይገባዋል፤ ይህንን ለማድረግ ደግሞ ምቹ አለልዎ!
የምቹ መተግበሪያን ዛሬውኑ በማውረድ፣ ወደ የፋይናንስ ግብዎን ለማሳካት የመጀመሪያውን አስፈላጊ እርምጃ አሁኑኑ ይውሰዱ።
በጣም ፈጣን፣ ቀላል እና ሁኔታዎን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተነደፈ ነው።