የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 22ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የጉባኤ ጥሪ
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)፣ 367(1) እና አንቀጽ 370 እንዲሁም በባንኩ መመሥረቻ ፅሑፍ አንቀፅ 17(1) እና 18(1) መሠረት
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 22ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም (እ.ኤ.አ ኦክቶበር 17
ቀን 2026) ከጠዋቱ 2፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በአዳማ ከተማ፣ ገልማ አባ ገዳ ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የተከበራችሁ የአክሲዮን ማህበሩ
ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተጠቀሰው ቦታ፣ ቀንና ሰዓት በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን
ያስተላልፋል፡፡
1. ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
1.1 የአክሲዮን ማህበሩ ስም፡- የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ.
1.2 የአክሲዮን ማህበሩ ዓይነት፡- በባንክ ሥራ ላይ የተሰማራ አክሲዮን ማህበር
1.3 የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 02፣ የቤ/ቁ. 3020
1.4 የአክሲዮን ማህበሩ ድረ-ገፅ፡- https://.coopbankoromia.com.et
1.5 የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር:- KK/AA/3/0001918/2004
1.6 የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ(ካፒታል)፡- 12,800,000,000.00
1.7 የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) ፡- 12,800,000,000.00
2. የ22ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
2.1 የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፣
2.2 አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅ፣
2.3 እ.ኤ.አ. የ2025/26 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ መወሰን፣
2.4 እ.ኤ.አ. የ2025/26 የባንኩን የውጭ ኦዲተሮች ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ መወሰን፤
2.5 እ.ኤ.አ. ለ2026/27 የውጭ ኦዲተሮችን መሾም እና ክፍያቸውን መወሰን፣
2.6 እ.ኤ.አ. የ2025/26 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ክፍያን እና የ2026/27 ወርሃዊ አበል መወሰን፤
2.7 እ.ኤ.አ. በ2025/26 ሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ ተወያይቶ መወሰን፡
ማሳሰቢያ
• በጉባኤው መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻቸው ሥልጣን ባለው የመንግሥት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሠነድ ዋናውና ፎቶኮፒ በመያዝ
ወይም በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባዔው ከመካሄዱ ከሶስት (3) ቀናት በፊት አዲስ አበባ ከተማ፣ ቦሌ ክ/ከተማ፣ ቦሌ ሩዋንዳ አከባቢ በሚገኘው
የባንኩ ዋና መ/ቤት 7ኛ ፎቅ የባለአክሲዮኖች ግንኙነት ክፍል ወይም በአቅራቢያቸው በሚገኘው የባንኩ ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ በባንኩ
የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባኤው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት
የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በማናቸውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
• የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ ብሄራዊ መታወቂያ
(ፋይዳ)፣ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ዋናውና ኮፒ በመያዝ በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላሉ:: እንዲሁም ትውልደ
ኢትዮጵያውያን የሆኑ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የባንኩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት የኢትዮጵያ
ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
• ድርጅትን (የኅብረት ሥራ ማኅበርን ወይም ሌላ ድርጅትን) ወክሎ የሚቀርብ ተወካይ የድርጅቱ/የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ
ይዞ/ይዛ መቅረብ ያለበት/ያለባት ሲሆን፤ አለዚያም በባንኩ የውክልና መስጫ ቅጽ መሠረት ውክልና ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
• በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንኮች አስተዳደር መመሪያ ቁጥር SBB/91/2024 አንቀጽ 20(3) መሰረት የባንኩ የቦርድ አባላት እና የባንኩ ሠራተኞች
ባለአክሲዮኖችን በመወከል ጉባኤው ላይ መሳተፍ አይችሉም፡፡
• ተወካዮች የሚቀበሉት የውክልና መጠን የራሳቸውን አክሲዮን ጨምሮ ከባንኩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ ከአስር በመቶ (10%) መብለጥ የለበትም፡፡
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ.
የዳይሬክተሮች ቦርድ