የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 20ኛ መደበኛ እና 11ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የጉባኤ ጥሪ
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ህዳር 13 እና 19 2017 እና የሪፖርተር ጋዜጣ ህዳር 15 እና 22 2017 ዓ.ም በተላለፈው ጥሪ መሰረት፣ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)፣ 367(1) እና
አንቀጽ 370 እንዲሁም በባንኩ መመሥረቻ ፅሑፍ አንቀፅ 17(1) እና 18(1) መሠረት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 20ኛ መደበኛ እና 11ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ
ጉባኤ እ.ኤ.አ ቅዳሜ ዴሴምበር 21/2024 (ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም) ከጠዋቱ 2፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በአዳማ ከተማ፣ አባ ገዳ አደራሽ ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የተከበራችሁ
የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተጠቀሰው ቦታ፣ ቀንና ሰዓት በጉባኤው ላይ እንድትገኙልን የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል::
- ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
ማህበሩ ስም፡- የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ.
የማህበሩ ዓይነት፡- በባንክ ስራ ላይ የተሰማራ አክሲዮን ማህበር
የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 02፣ የቤ/ቁ. አዲስ
የባንኩ ድረ-ገፅ፡- https://www.coopbankoromia.com.et
የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር:- KK/AA/3/0001918/2004
አክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ(ካፒታል)፡- 12,800,000,000.00
አክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) ፡- 11,253,744,600.00
- የ11ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳ
2.1 የባንኩን የመመስረቻ ጽሑፍ ለማሻሻል በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- የ20ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
3.1 እ.ኤ.አ. ከታህሳስ 01/2023 እስከ ህዳር 30/2024 ድረስ የተደረጉ የአክሲዮኖችን ዝውውር ማጽደቅ፣
3.2 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የጥቆማና ምርጫ አፈፃፀም ፖሊሲ እና የአሰራር ስርዓትን ተወያይቶ ማጽደቅ፣
3.3 ጊዜያዊ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የጥቆማና አስመራጭ ኮሚቴ መምረጥ፣
3.4 እ.ኤ.አ. የ2023/24 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ መወሰን፣
3.5 እ.ኤ.አ. የ2023/24 የባንኩን የውጭ ኦዲተሮች ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ መወሰን፣
3.6 እ.ኤ.አ. ለ 2024/25 የውጭ ኦዲተሮችን መሾም እና ክፍያቸውን መወሰን፣
3.7 የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ምርጫ ማከናወን፣
3.8 እ.ኤ.አ. በ2023/24 ሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
3.9 እ.ኤ.አ.የ2023/24 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ክፍያን እና የ2024/25 ወርሃዊ አበል መወሰን፡
- ማሳሰቢያ
4.1. በጉባኤው መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻቸው ሥልጣን ባለው የመንግሥት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሠነድ ዋናውና ፎቶኮፒ
በመያዝ ወይም በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባዔው ከመካሄዱ ከሶስት(3) ቀናት በፊት አዲስ አበባ፣ቦሌ መንገድ ቦሌ ሩዋንዳ አከባቢ በሚገኘው
የባንኩ ዋና መ/ቤት 7ኛ ፎቅ አክሲዮን አስተዳደር ክፍል ወይም በአቅራቢያቸው በሚገኘው የባንኩ ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ በባንክ
የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባኤው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት
የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በማናቸውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ
መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
4.2. የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ
ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውና ኮፒ በመያዝ በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላሉ:: እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የውጭ ሀገር ዜግነት
ያላቸው የባንኩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ (ቢጫ ካርድ)
ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
4.3 ድርጅትን (የኅብረት ሥራ ማኅበርን ወይም ሌላ ድርጅትን) ወክሎ የሚቀርብ ተወካይ የድርጅቱ/የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ
ይዞ መቅረብ ያለበት ሲሆን፤አለዚያም በባንኩ የውክልና መስጫ ቅጽ መሠረት ውክልና ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
4.4 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንኮች አስተዳደር መመሪያ ቁጥር SBB/91/2024 አንቀጽ 20(3) መሰረት የባንኩ የቦርድ አባላት እና የባንኩ ሰራተኞች
ባላአክሲዮኖችን በመወከል ጉባኤው ላይ መሳተፍ አይችሉም፡፡
4.5 ተወካዮች የሚቀበሉት የውከልና መጠን የራሳቸውን አክሲዮን ጨምሮ ከባንኩ የተፈረም ዋና ገንዘብ ከአስር በመቶ መብለጥ የለበትም፡
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ