Month: December 2024

በባንኩ መመስረቻ ጽሑፍ ላይ የቀረበ የማሻሻያ ሀሳብ ረቂቅ

  1. የማሻሻያው ምክንያት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም ባደረገው የህግ እና ቁጥጥር ሪፎርም ባንኮች የተለያዩ የአሰራር እና አስተዳደር ለውጦችን እንዲያደርጉ የሚያስገድዱ ድንጋጌዎችን የያዙ መመሪያዎችን አውጥቷል፡፡ በተለይም የባንክ ቦርድ አወቃቀር፣ ኃላፊነቶችና ተግባራት እንዲሁም በአጠቃላይ በባንክ አስተዳደርና አመራር ውስጥ የሚሳተፉ አካላት ተግባር እና ኃላፊነትን በተመለከተ ሰፊ ለውጦች ተደርጓል፡፡ በመሆኑም የባንኩን መመስረቻ ጽሑፍ መመሪያዎቹ ይዘው ከመጡት ለውጦች ጋር በተጣጣመ መልኩ ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የሚከተሉት የማሻሻያ ሀሳቦች ቀርበዋል፡፡

  1. ማሻሻያ የተደረገባቸው አንቀጾች ዝርዝር

1.አንቀጽ 21፡ የጥቅም ግጭት

  • የተደረገው ማሻሻያ- የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ (7) ተጨምሯል፡፡

’7. ባንኩ ተፈጻሚነት ባለው ህግ አግባብ የጥቅም ግጭትን የሚመዘገብበት መዝገብ ይይዛል፡፡’’

  1. አንቀጽ 23፡ የባንኩ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ስልጣንና ተግባራት
  • የተደረገው ማሻሻያ- በመመስረቻ ጽሑፉ አንቀጽ 23 (3) (መ) እና (ሠ) ላይ የሚከተለው ማሻሻያ ተደርጓል፡-

‘’መ.  በዳይሬክተሮች ቦርድ ተዘጋጅቶ የቀረበለትን የቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ አፈፃፀም ፖሊሲና የአሰራር ስነ-ስርዓት ያጸድቃል፣ ያሻሽላል፡፡

ሠ. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ በሚካሄድበት ጉባዔ ዕለት የምርጫ ሂደቱን የሚያስፈጽም ጊዜያዊ የቦርድ        የጥቆማና አስመራጭ ኮሚቴ አባላትን በመምረጥ ኮሚቴው እንዲቋቋም ያደርጋል።’’

  1. አንቀጽ 26- የዳይሬክተሮች ቦርድ
  • የተደረገው ማሻሻያ- ነባሮቹ ንዑስ አንቀጽ 26(1) እና 26(6) ላይ የሚከተለው ማሻሻያ ተደርጓል፡፡
  1. ‘’ባንኩ በመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው በሚመረጡ፣ በአንድነት ሥራቸውን በሚያካሄዱና ለባንኩ እንደራሴ በሚሆኑ 12 (አስራ ሁለት) አባላት ባሉት አንድ የዳይሬክተሮች ቦርድ ይመራል፡፡’’
  2. ቦርዱ ከአባላቱ መካከል ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ ይመርጣል፤ እንደዚሁም ተፈጻሚነት ባለው ህግ አግባብ ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ኮሚቴዎችን ያቋቁማል፡፡”

4.አንቀጽ 28፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ አወቃቀር

  • የተደረገው ማሻሻያ- በነባሮቹ ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 ላይ ማሻሻያ የተደረገባቸው ሲሆን፣ ንዑስ አንቀጽ 3 ከመመስረቻ ጽሑፉ እንዲወጣ ተደርጎ 3 አዳዲስ ንዑስ አንቀጾች እንደሚከተለው ተጨምረዋል፡፡
  1. ‘’የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ከባንኩ ባለአክሲዮኖች፣ የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚና ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎችን (ሲኒየር ኤክሰኪቲቭ አፊሰሮች) ጨምሮ ከባንኩ ሠራተኞች እና ገለልተኛ ከሆኑ ዕጩዎች ውስጥ የተመረጡ ዳይሬክተሮችን ያካትታል፡፡
  2. የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ዕድገት ደረጃ፣ የስራውን ውስብስብነት እና የአደጋ ተጋላጭነት መገለጫን በሚመጥን፣ ስራው የሚፈልገውን የእውቀትና ሙያ ስብጥርን ባገናዘበ፣ እንዲሁም ልዩነትን አካታች በሆነ መልኩ መዋቀር አለበት፡፡ የሞያ/እወቀት ስብጥሩ የባንክ፣ የፋይናንስ፣ የሂሳብ አያያዝ፣ የማኔጅመንት፣ የኢኮኖሚክስ፣ የህግ፣ የንግድ አስተዳደር፣ የኦዲት፣ የመረጃ ቴክኖሎጂ፣ የኢንቨስትመንት አመራር፣ እና የዘላቂነት (ሰስቴናቢሊቲ) ሙያዎችን ያካትታል፡፡
  3. የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ፡

ሀ. ተጽዕኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች ብቻ የሚጠቆሙ እና የሚመረጡ 4 (አራት) ዳይሬክተሮች፤

ለ. በሁሉም የባንኩ ባለአክሲዮኖች የሚጠቆሙ እና የሚመረጡ 4 (አራት) ዳይሬክተሮች፤ እና

ሐ. ስራ ላይ ባለው የዳይሬክተሮች ቦርድ ተመልምለው በሚቀርቡ እና በሁሉም የባንኩ ባለአክሲዮኖች የሚመረጡ 4 (አራት) ገለልተኛ የሆኑ ዳይሬክተሮችን በማካተት ይዋቀራል፡፡

  1. የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አወቃቀር የፆታ ውክልናን ያረጋገጠ መሆን አለበት፤ በዚሁ መሰረት ከአጠቃላይ የባንኩ ቦርድ አባላት ውስጥ ቢያንስ ሁለቱ (2) ሴቶች መሆን አለባቸው፡፡
  2. የባንኩን ዋና ስራ አስፈጻሚን እና ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎችን (ሲኒየር አክሰኪቲቭ አፊሰሮችን) ጨምሮ እጅግ ቢበዛ ሁለት (2) የባንኩ ሠራተኞች በቦርድ አባልነት ሊመረጡ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን የባንኩ ጸሐፊ የቦርድ አባል ሆኖ መመረጥ አይችልም፡፡

5.አንቀጽ 29፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሥልጣንና ተግባራት

  • የተደረገው ማሻሻያ- ንዑስ አንቀጽ 29 (11) በሁለት ንዑስ አንቀጾች ተከፍሎ (11 እና 12)፣  ንዑስ አንቀጽ (12)፣ (16)፣ (19) እና (22) ላይ ደግሞ ማሻሻያ ተደርጎዋል፤ እንዲሁም 4 አዳዲስ ንዑስ አንቀጾች ተጨምረዋል፡፡
  1. ‘’የቦርዱ የጥቆማ እና የስራ ዋጋ ኮሚቴ (Nomination and Remuneration Committee) በሚያቀርበው የውሳኔ ሀሳብ መሠረት የባንኩ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎች ሹመት፣ ምደባና ስንብት ላይ ይወስናል፡፡
  2. የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ በሚያቀርበው የውሳኔ ሀሳብ መሠረት የባንኩ ፀሐፊ ሹመት፣ ምደባና ስንብት ላይ ይወስናል፡፡
  3. ተፈጻሚነት ባለው ህግ መሰረት ሀላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት የሚያስፈልጉትን የተለያዩ ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎችን ያቋቁማል፣ በአግባቡ መስራታቸውንም ያረጋግጣል፡፡
  4. ግልጽ የሆነ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ አፈፃፀም ፖሊሲ እና የአሰራር ስነስርዓትን አዘጋጅቶ እንዲጸድቅ ለመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ያቀርባል፡፡
  5. በዚህ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 23 (3)(ቀ) ስር የተቀመጠው የመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ተፈጻሚነት ባለው ሕግና በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት በባንኩ እና ከባንኩ ጋር ቅርበት ባላቸው ሰዎች ወይም ድርጅቶች መካከል የሚደረግ ስምምነትን ስምምነቱ ከመፈጸሙ በፊት በቅድሚያ ይፈቅዳል፣ ከፈቀደ በኋላም ወዲያውኑ ለኦዲተሮች ያሳውቃል፣
  6. ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ሲል በሚያደርገው የአይነት ወይም የገንዘብ ስጦታ ላይ ይወስናል፤ እንዳስፈላጊነቱም ባንኩ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የሚያስችሉ እና በዚሁ ዙሪያ የሚሰሩ ፋውንዴሽኖችን አንዲያቋቁም በሚቀርብ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ይወስናል፣

ተጨማሪ የዳይሬክተሮች ቦርድ ኃላፊነትና ተግባራት፡

  1. ‘’ባንኩ በልዩ ልዩ የፋይናንስና ተያያዥ ስራ ዘርፎች ላይ በማተኮር የሚሰሩ ተቀጥላ ኩባንያዎችን እንዲያቋቁም በሚቀርብ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ይወስናል፤
  2. የባንኩን የስነ-መግባር መርሆች እና እሴቶችን (Corporate Culture and Value) ይቀርጻል፤ ለሚመለከታቸው የባንኩ አካላት በማሳወቅ ስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
  3. ባንኩ ከዘላቂነት (Sustainability) ጋር ለተያያዙ የአደጋ ስጋቶች እና እድሎች (sustainability-related risks and opportunities) በሚሰጠው ምላሽ ላይ ቁጥጥር ያደርጋል፤ የባንኩ ከፍተኛ አመራር እነዚህን የአደጋ ስጋቶችን እና እድሎችን ከመቆጣጠር አንጻር ያለውን ሚና እና ኃላፊነቶችን በግልጽ ያስቀምጣል፣
  4. የባለድርሻ አካላት ከባንኩ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እና ሂደቱን ይቆጣጠራል፤ እንዲሁም በባለድርሻ አካላቱ የሚነሱ ሀሳቦች እና ስጋቶች በባንኩ ስትራቴጂ ውስጥ መካተታቸውን ያረጋግጣል፣‘’
  1. አንቀጽ 30፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ
  • የተደረገው ማሻሻያ- ነባሮቹ ንዑስ አንቀጽ 3 እና 4 በማሻሻያው አዲስ ንዑስ አንቀጽ 4 ስር እንዲካተቱ ተደርጎ ሁለት አዳዲስ ንዑስ አንቀጾች (ንዑስ አንቀጽ 2 እና 4) እንደሚከተለው ተጨምረዋል፡፡

2.‘’የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ መሆን የሚችለው ባለአክሲዮን የሆነ ዳይሬክተር ነው፤ ከሠራተኛ የተመረጠ እና ገለልተኛ የሆነ ዳይሬክተር የቦርድ ሰብሳቢ መሆን አይችልም፤

  1. በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው ማኅበርን/ተቋምን ወክሎ የቦርድ አባል የሆነ ሰው የቦርድ ሰብሳቢ ሆኖ መመረጥ ይችላል፡፡ ሆኖም ተወካዩ ኃላፊነቱን ከተወ ወይም በኃላፊነቱ መቀጠል የማይችልበት ሁኔታ ከተፈጠረ በዚህ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 28(6) መሰረት ወካዩ ይሄንኑ ለባንኩ በጽሑፍ ለማሳወቅ እና ሌላ ተወካይ ለመመደብ ያለበት ሃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ በማህበሩ/በተቋሙ በተተኪነት የሚመደበው ተወካይ የቦርድ ሰብሳቢነቱን ቦታ የመውረስ መብት አይኖረውም፡፡ በመሆኑም ከኃላፊነቱ የለቀቀውን ሰብሳቢ የሚተካ ሌላ አባል በቦርዱ የሚመረጥ ይሆናል፡፡
  2. ሰብሳቢው በሕግ እና በዚህ መመስረቻ ጽሑፍ የተሰጡትን ስልጣን እና ተግባራት ይኖሩታል፡፡ ይህ ጠቅለል ያለ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ሰብሳቢው የሚከተሉ ኃላፊነቶች እና ተግባራት ይኖሩታል፡-

ሀ. የባንኩን ውጤታማነት በሚያረጋግጥ መልኩ ቦርዱን መምራት፣

ለ. በዳይሬክተሮች ቦርድና በጠቅላላ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችን ተግባራዊ ማድረግ፣

ሐ. ለዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሰባዎች አጀንዳ ማዘጋጀት ወይም እንዲዘጋጅ ማድረግ፤ የቦርድ ስብሰባዎችን መጥራት፣ በግልጽነት፣ የሀሳብ ነጻነትና ልዩነትን በሚያከብር እና ጥልቅ ውይይትንና ክርክርን በሚያበረታታ መልኩ ስብሰባውን መምራት፤

መ. በዳይሬክተሮች ቦርድ የተጠራውን ጠቅላላ ጉባዔ መምራት፡፡

  1. አንቀጽ 31 የዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሰባ እና ውሳኔ
  • የተደረገው ማሻሻያ- በንዑስ አንቀጽ 1 እና 3 ላይ ማሻሻያ የተደረገ ሲሆን፣ነባሩ ንዑስ አንቀጽ 5 ድንጋጌ ከመመስረቻ ጽሑፉ ወጥቶ በምትኩ ሌላ ድንጋጌ ተካቶዋል።
  1. ‘’የዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሰባ የሚያካሄድበትን ሁኔታ የሚደነግግ ደንብ ማውጣት አለበት፡፡ በዚሁ ደንብ ውስጥ በሚወሰን ቀን እና ቦታ ቢያንስ በሩብ ዓመት አንድ ጊዜ ስብሰባውን ማካሄድ ይኖርበታል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ ሰብሳቢው ሌሎች የዳይሬክተሮች ቦርድን ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፡፡

3.ቦርዱ በቪድዮ ኮንፈረንስ ወይም ሌላ የኤሌክትሮኒክ መገናኛ ዘዴ በመጠቀም አስቸኳይ ስብሰባዎችን ማካሄድ ይችላል፡፡ የኤሌክትሮኒክ የመገናኛ ዘዴው የተሰብሳቢዎችን ማንነት ለመለየት የሚያስችል እንዲሁም ውጤታማ ተሳትፎን የሚያረጋግጥ፣ ቢያንስ የተሳታፊዎችን ድምጽ ሳይቆራረጥ የሚያስተላልፍ፣ ምስጢራዊነትን ለመጠበቅ የሚያስችል እና ተሰብሳቢዎቹ በአንድ ጊዜ መሳተፍ እንዲችሉ የሚፈቅድ መሆን አለበት፡፡

5.የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት በእያዳንዱ የስብሰባ አጀንዳ ላይ ለመወያየት የሚያስችላቸውን በቂ ቅድመ ዝግጅት አድርገው ስብሰባው ላይ መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡’’

  1. አንቀጽ 33 ለባንኩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች መዝገብ
  • የተደረገው ማሻሻያ- ንዑስ አንቀጽ 33(2) እና (6) ላይ የሚከተለው ማሻሻያ ተደርጓል፡፡

‘’2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ስር የተዘረዘሩት የተፈጥሮ ሰዎች የትዳር አጋር ወይም ከነዚህ ሰዎች ጋር ተፈፃሚነት ባለው ሕግ መሰረት የስጋና የጋብቻ ዝምድና ያላቸው ሰዎች ከባንኩ ጋር ቅርበት ካላቸው ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ይካተታሉ፡፡

6.ባንኩ ለባንኩ ቅርበት ካላቸው ሰዎች መዝገብ በተጨማሪም እያንዳንዱ ከባለአክሲዮኖች የተመረጠ የባንኩ የቦርድ አባል ያለውን የአክሲዮን ብዛትና ዋጋቸውን የሚያመለክት መዝገብ በዋናው መስሪያ ቤቱ ይይዛል፡፡’’

  1. አንቀጽ 35፡ የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሥልጣንና ተግባር
  • የተደረገው ማሻሻያ- አንቀጽ 35(6) በተለያዩ ሁለት ንዑስ አንቀጾች  (35.6) እና (35.7) ተከፍሎ የሚከተለው ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡

 ‘’6. ዕጩ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎችን መልምሎ ሹመታቸውን በዋናው ቦርድ እንዲያጸድቅ ለቦርዱ የጥቆማ እና የስራ ዋጋ ኮሚቴ(Nomination and Remuneration Committee) ያቀርባል፣

7.የባንኩን ፀሐፊ በመመልመል ሹመቱ እንዲጸድቅ ለቦርድ ያቀርባል፡፡’’

  1. አንቀጽ 37 የባንኩ ፀሐፊ ሥልጣንና ተግባር
  • የተደረገው ማሻሻያ- ነባሩ ንዑስ አንቀጽ 37(8) ላይ ማሻሻያ ተደርጎ ሌላ ሶስት አዳዲስ ንዑስ አንቀጾች ተጨምረዋል፡፡

‘’8. የባንኩን የባለአክሲዮኖች መዝገብ፣ የዳይሬክተሮች መዝገብ፣ ከባንኩ ጋር ቅርበት ያላቸው ሰዎች መዝገብ እና የጥቅም ግጭት መዝገብን በትክክል ማደራጀት፣ በአግባቡ መያዝ እና መዝገቦቹ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን ያካተቱ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣

ተጨማሪ የጸሐፊው ስልጣን እና ተግባራት፡

  1.     የባንኩን መልካም አስተዳደር እና የመልካም አስተዳደር መስፈርቶች መሟላታቸውን በቅርበት

         መከታተል፣  

  1. የቦርድ እና የኮሚቴ ስብሰባዎችን የጊዜ መረኃ ግብር ማዘጋጀት፣
  2. የቦርድ አባላት ውጤታማ የሆነ የአቅም ግንባታ እና ስልጠና መውሰዳቸውን ማረጋገጥ፣’’
  1. አንቀጽ 39 (9)፡ የባንኩ ኦዲተሮች ተግባር፣ ኃላፊነት እና ስልጣን
  • የተደረገው ማሻሻያ- በንዑስ አንቀጽ 39(9) ላይ የሚከተለው ማሻሻያ ተደርጓል፡፡

‘’9. በባንኩ እና ከባንኩ ጋር ቅርበት ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግን ስምምነት አስመልክቶ በዚህ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 23 (3) (ቀ) እንዲሁም በንግድ ሕጉ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች መሰረት ውሳኔ ለመስጠት ይረዳ ዘንድ ስለውሉ ሁኔታ፣ የተፈፀመውን ክፍያ አይነትና መጠን፣ እንዲሁም ለጥቅም ግጭት ምክንያት የሆነውን የቅርበት ሁኔታ የሚገልፅ በቂ መረጃ በማካተት የጽሑፍ ሪፖርት ለጠቅላላ ጉባኤ ማቅረብ፣’’

ከላይ በቀረበው መልኩ በያንዳንዱ አንቀጾች ላይ የተደረገው ማሻሻያ እንደተጠበቀ ሆኖ የተደረገው ማሻሻያ በንዑስ አንቀጾች ቅደም ተከተል ላይ ለውጥ ያስከተለባቸው አንቀጾችን በተመለከተ የሀሳብ ፍሰቱን በጠበቀ እና ተያያዥነታቸውን ባገናዘበ መልኩ ተገቢው የቅደም ተከተል ማስተካከያ ተደርጎባቸዋል፡፡ አንቀጽ 28፣ 29፣ 30 እና 37 በዚሁ መሰረት የንዑስ አንቀጾች ቅድመ ተከተል ማሻሻያ እና ሽግሽግ የተደረገባቸው አንቀጾች ናቸው፡፡

 

 

 


Wixinee Barreeffama Hundeeffamaa Baankichaa Fooyyessuuf Dhiyaate.

 

  1. Sababa fooyya’iinsaa

Baankiin Biyyoolessaa Itiyoophiyaa riifoormii seeraa fi to’annoo Waxabajjii bara 2016 taasiseen qajeelfamoota baankonni jijjiirrama hojmaataa fi bulchiinsaa akka taasisan dirqisiisan baasee jira. Keessattuu gurmaa’insa, ittigaafatamummaa fi gahee hojii boordii baankii fi qaamota bulchiinsaa baankii keessatti hirmaatanii ilaalchisee jijjiirrama bal’aa taasisee jira. Kanaafuu, barreeffama hundeeffamaa baankichaa jijjiirramoota dhufan waliin bifa wal simuun fooyyessuun barbaachisaa ta’ee waan argameef wixineen fooyya’iinsaa armaan gadii kun dhiyaatee jira.

  1. Keewwatoota Fooyya’an

1) Keewwata 21: Walitti Bu’iinsa Dantaa

Fooyya’iinsa taasifame- Keewwatni xiqqaa haaraan armaan gadii dabalamee jira.

‘‘7. Baankichi bu’uura seera raawwatiinsa qabuutiin galmee walitti bu’iinsa dantaa irratti galmeessu ni qabaata.’’

2) Keewwata 23: Aangoo fi Gahee Hojii Yaa’ii Waliigalaa Idilee

Fooyya’iinsa taasifame- Barreeffama hundeeffamaa keewwata 23(d) fi (e) irratti fooyya’iinsi armaan gadii taasifamee jira.

‘‘d) Poolisii fi Qajeelfama adeemsa hojmaata eeruu fi filannoo miseensota boordii, boordii daarektarootaatiin qopha’ee dhiyaateef ni mirkaneessa, ni fooyyessa.

“e) Guyyaa yaa’ii waliigalaa filannoon miseensota boordii daarektarotaa itti gaggeeffamu irratti Miseensota Koree Yeroo Eeruu fi Filachiistuu Boordii, adeemsa filannoo boordii raawwachisu filachuun, korichi akka hundeeffamu ni taasisa.’’

3) Keewwata 26: Boordii Daayrektarootaa

Fooyya’iinsa taasifame- Keewwatoota xiqqaa 26(1) fi 26(6) irratti fooyya’iinsi armaan gadii taasifamee jira.

  1. Baankichi boordii daayrektarootaa tokko, miseensota yaa’ii waliigalaa idileetiin filataman kudha lama (12) of keesssa qabu, tokkummaan hojii isaanii gaggeessanii fi bakka bu’oota baankichaa ta’aniin hogganama.
  2. Boordichi walitti qabaa fi itti aanaa walitti qabaa miseensota isaa keessaa ni filata; akkasumas koreewwan hojii isaatiif barbaachisoo ta’an bu’uura seera raawwatiinsa qabuutiin ni hundeessa.’’

4) Keewwata 28: Gurmaa’insa Boordii Daayrektarootaa

Fooyya’iinsa taasifame- Keewwatoota xiqqaa 1 fi 2 irratti fooyya’iinsi kan taasifame yoo ta’u, keewwanni xiqqaan 3 barreeffama hundeeffamaa keessaa akka bahu taasifamee jira. Dabalataan, keewwatoonni xiqqaan haaraan sadi (3) dabalamanii jiru.

  1. ‘’Boordiin daayrektarootaa baankichaa miseensota abbootii aksiyoonaa, hojii gaggeessaa olaanaa fi itti aantota hojii gaggeessaa olaanaa dabalatee hojjattoota baankichaa, fi kaadhimamtoota walabaa keessaa daayrektaroota filataman ni hammata.
  2. Boordiin daarektarootaa baankichaa sadarkaa guddinaa, ulfaatina hojii fi saaxilamummaa balaa baankichaa (Risk Profile) haala madaaluun, beekumsaa fi ogummaa gara garaa hojichi barbaadu haala ilaalcha keessa galcheen, akkasumas hirmaachisaa bifa taheen gurmaa’uu qaba. Ogummaa fi beekumsi hojichaaf barbaachisu kunnen baankiingii, faayinaansii, qabiinsa herreegaa, bulchiinsa, qor-diinagdee (economics), seera, bulchiinsa daldalaa, odiitii, teeknolojii odeeffannoo, bulchiinsa inveestmantii fi ogummaa itti fufiinsaa (sustainability) kan dabalatu taha.
  3. Boordiin daayrektaroota baankichaa:
  4. Daayrektaroota 4 (afur) abbootii aksiyoonaa dhiibbaa uumtota hin taane eeramanii fi filataman,
  5. Daayrektaroota 4 (afur) abbootii aksiyoonaa hundaan eeramanii fi filataman, fi
  6. Daayrektaroota walabaa 4 (afur) boordii daayrektarootaa hojiirra jiruun calalamuun dhiyaatanii fi abbootii aksiyoonaa hundaan filataman haammachuun ni gurmaa’a.
  7. Gurmaa’insi boordii daayrektaroota baankichaa bakka bu’ummaa koorniyaa kan mirkaneessu ta’uu qaba; bu’uuruma kanaan miseensota waliigalaa boordii daayrektaroota baankichaa keessaa yoo xiqqaate lama (2) dubartoota ta’uu qabu.
  8. Hojii gaggeessa olaanaa fi itti aantota hojii gaggeessaa olaanaa dabalatee yoo baay’ate hojjattootni baankichaa lama (2) miseensummaa boorditiif filatamuu danda’u. Haa ta’u malee barreessaan baankichaa miseensa boordii ta’uun filatamuu hin danda’u.

5) Keewwata 29: Aangoo fi Gehee Hojii Boordii Daayrektarootaa

Fooyya’iinsa taasifame- Keewwanni xiqqaan 29(11) keewwattoota xiqqaa lamatti kan adda bahe yoo tahu, keewwattoota xiqqaa (12), (16) (19) fi (23) irratti fooyya’iinsi taasifamee jira; akkasumas keewwatoonni xiqqaan haaraan afur(4) dabalamanii jiru.

‘’11. Muudama, ramaddii fi hojiirraa gaggeeffamuu itti aantota hojii gaggeessaa olaanaa irratti yaada murtoo koreen eeruu fi kaffaltii hojii (Nomination and Remuneration Committee) boordii dhiyeessurratti hundaa’un ni murteessa.

  1. Muudama, ramaddii fi hojiirraa gaggeeffamuu barreessaa baankichaa irratti yaada murtoo hojii gaggeessaa olaanaan baankichaa dhiyeessurratti hundaa’un ni murteessa.
  2. Koreewwan yeroo fi dhaabbii itti gaafatamummaa isaa haalaan bahuuf isa barbaachisan bu’uura seera raawwatiinsa qabuutin ni hundeessa; sirnaan hojjechuu isaaniis ni mirkaneessa.

17.Poolisii fi Qajeelfama adeemsa hojmaata eeruu fi filannoo miseensota boordii daayreektarootaa ifa ta’e qopheessuun akka ragga’uuf yaa’ii waliigalaa idileetiif ni dhiyeessa.

20.Aangoon yaa’ii waliigalaa idilee barreeffama hundeeffamaa kana keewwata 23(3)(h) jalatti tumame akkuma jirutti ta’ee, bu’uura seera raawwatiinsa qabuu fi qajeelfama baankii biyyoolessaatiin waliigalteen baankichaa fi namoota yookiin dhaabbilee baankicha waliin hidhata qaban gidduutti taasifamu waliigaltichi raawwatamuu isaatiin dura ni hayyama; erga hayyamee boodas battalatti odiitaroota alaa ni beeksisa.

23.Itti gaafatamummaa hawaasummaa isaa baahachuuf deeggarsa meeshaalee ykn maallaqaa baankichi taasisu irratti ni murteessa, barbaachisaa tahee yoo argames baankichi Faawundeeshinii bifa itti fufiinsa qabuun itti gaafatamummaa hawaasummaa isaa bahachuuf isa dandeessisu hundeessuuf yaada murtee dhiyaatu irratti ni murteessa.’’

Aangoo fi Gahee Hojii Boordii Daarektarootaa Akka Haaraatti Dabalaman

24.Baankichi kubbaaniyaawwan moggee (subsidiary company) hojiilee faayinaansii adda addaa fi isaan hidhata qaban irratti fuulleffachuun hojjetan hundeessuuf yadaa murtee dhiyaatu irratti ni murteessa.

  1. Qajeeltoowwan naamusaa fi duudhaalee baankichaa (corporate culture and value) ni boca, qaama baankichaa dhimmi ilaallatu beeksisuun hojiirra akka oolan ni taasisa,
  2. Tarkaanfiwwan baankichi yaaddowan balaafii carraawwan itti fufiinsaan wal qabatan (sustainability-related risks and opportunities) ilaachisee fudhatu fi akkasumas gama kanaan gahee fi itti gaafatamummaa hoggansi olaanaa baankichaa qabu ifatti ni kaa’a, ni too’ata,
  3. Walitti dhufeenya qooda fudhattoonni baankicha waliin qabanii fi adeemsa isaa ni to’ata; akkasumas yaadotaa fi sodaawwan qooda fudhattoota irraa ka’an tarsiimoo baankichaa keessatti haammatamuu isaanii ni mirkaneessa’’

6) Keewwata 30: Walitti Qabaa Boordii Daayrektarootaa

Fooyya’iinsa taasifame- keewwatoonni xiqqaan haaraan lama (keewwatoota xiqqaa 2 fi 3) kan dabalaman yoo tahu, keewwatoonni xiqqaan 3 fi 4 keewwata xiqqaa 4 jalatti akka hammataman taasifamee jira.

2.”Walitti qabaa boordii baankichaa ta’uun filatamu kan danda’u daayrektara abbaa aksiyoonaa ta’edha. Daayrektarri hojjataa keessaa filatamee fi daayirektarri walabaa walitti qabaa boordii ta’ee filatamuu hin danda’u.

  1. Namni waldaa/dhaabbata mirgi namummaa seeraan kennameef bakka bu’uun miseensa boordii ta’e walitti qabaa boordii ta’ee filatamuu ni danda’a. Haa ta’u malee, bakka bu’aan kun itti gaafatamummaa isaa yoo dhiise yookiin haalli itti gaafatamummaa isaan itti fufuuf isa hin dandeessisne yoo uumame, bu’uura barreeffama hundeeffama kana keewwata 28(6)tiin bakka buusaan kanuma barreeffamaan baankicha beeksisuu fi bakka bu’aa biraa bakka buusuuf itti gaafatamummaan irra jiraatu akkuma jirutti ta’ee, namni waldichi/dhaabbatichi bakka buusuun ramadu iddoo walitti qabaa boordii dhaaluuf mirga hin qabaatu. Kanaafuu, boordichi miseensa biraa walitti qabaa Itti gaafatamummaa isaa gadi lakkise bakka bu’u kan filatu ta’a.
  2. Walitti qabaan Boordii aangoo fi gahee hojii seeraa fi barreeffama hundeeffamaa kanaan kennameef ni qabaata. Ibsi waliigalaa kuni akkuma jirutti ta’ee walitti qabaan itti gaafatamummaa fi gahee hojii armaan gadii ni qabaata:
    1. Akkaataa bu’aa qabeessummaa baankichaa mirkaneessuun boordii hogganuu qaba.
    2. Murtiiwwan boordii daayrektarootaa fi yaa’ii waliigalaatiin darban hojiirra oolchuu.
    3. Ajandaa marii walgahiiwwan boordii daayrektarootaatiif qopheessuu yookiin akka qophaa’u taasisuu, walgahiiwwan boordii waamuu.
    4. Yaa’ii waliigalaa boordii daayrektarootaatiin waamame dursuu.

7) Keewwata 31: Walgahii fi Murtoo Boordii Daayrektarootaa

Fooyya’iinsa taasifame-Keewwattoota xiqqaa 1 fi 3 irratti fooyya’iinsi kan taasifame yoo ta’u, tumaan keewwata xiqqaa 5 jala ture barreeffama hundeeffamaa keessaa bahee bakka isaa tumaan biraa bakka bu’ee jira.

1.’Boordiin daayrektaroota dambii haala walgahiin boordii ittiin gaggeeffamu baasuu qaba. Boordiin kurmaana waggaatti yoo xiqqaate yeroo tokko guyyaa fi iddoo dambii kana keessatti murtaa’utti walgahii idilee gaggeessuu qaba. Walitti qabaan boordii yeroo barbaachisaa ta’ee argametti walgahii boordii daayrekterootaa kan biroo waamuu ni danda’a.

3.Boordichi walgahii ariifachiisaa viidiyoo koonfransiidhaan yookiin tooftaa qunnamtii elektrooniksii kan biraa fayyadamuun gaggeessuu ni danda’a. Tooftaan qunnamtii elektrooniksiii kun eenyummaa hirmaattotaa adda baasuuf kan dandeessisu, akkasumas hirmaannaa bu’aa qabeessa taasisuu kan dandeessisu, yoo xiqqaate sagalee hirmaattotaa osoo addaan hin kutin kan dabarsu, iccitii eeguuf kan dandeessisuu fi hirmaatttoonni al-tokkotti hirmaachuu akka danda’an kan dandeessisu ta’uu qaba.

  1. Miseensonni boordii daayrektarootaa qophii gahaa tokkoon tokkoon ajandaa walgahii irratti mari’achuuf isaan dandeessisu taasisuun walgahii irratti argamuu qabu.’’

8) Keewwata 33: Galmee Namoota Baankicha Waliin Hidhata Qabanii

Fooyya’iinsa taasifame- Keewwata xiqqaa 33(2) fi (6) irratti fooyya’iinsi armaan gadii taasifamee jira.

  1. ‘‘Abbaan manaa yookiin haati manaa namoota uumamaa keewwata kana keewwata xiqqaa 1 jalatti tarreeffamanii yookiin namoota kana waliin bu’uura seera raawwatiinsa qabuun firummaa dhiigaa fi gaa’ilaa namoonni qaban tarree namoota baankicha waliin hidhata qabanii keessatti haammatamu.
  2. Galmee namoota baankicha waliin hidhata qabaniitti dabalataan baankichi galmee baay’inaa fi gatii aksiyoona tokkoon tokkoon miseensonni boordii abbootii aksiyoonaa keessaa filataman qaban agarsiisu waajjira muummee isaatti ni qabata.’’

9) Keewwata 35: Aangoo fi Gahee Hojii Hoji-Gaggeessaa Olaanaa Baankichaa

Fooyya’iinsa taasifame- Keewwanni 35(6) keewwattoota xiqqaa lamatti hiramuun fooyya’iinsi armaan gadii taasifamee jira.

‘’6. Kaadhimamtoota Itti aantota hojii gaggeessaa olaanaa calaluun muudama isaanii Boordiitti dhiyeessun akka raggasisuuf koree eeruu fi kaffaltii hojii boordiif ni dhiyeessa.

  1. Barreessaa baankichaa calaluun muudamni isaa akka ragga’uuf boordiif ni dhiyeessa’’

10) Keewwata 37: Aangoo fi Gahee Hojii Barreessaa Baankichaa

Fooyya’iinsa Taasifame- Keewwata xiqqaa 37(8) irratti fooyya’iinsi taasifamee, keewwatoonni haaraa xiqqaan sadi dabalamanii jiru.

‘’8. Galmeewwan abbootii aksiyoonaa, daayrektarootaa, namoota baankii waliin hidhata qabanii fi walitti bu’iiinsa dantaa baankichaa karaa sirriin qindeessuu, sirnaan qabuu fi galmeewwan kunneen odeeffannoo waayitaawaa fi sirrii ta’e qabachuu isaanii mirkaneessuu,’’

Aangoo fi Hojii Dabalataa Barreessaa

  1. Bulchiinsa gaarii baankichaa fi ulaagaaleen bulchiinsa gaarii guutamuu isaanii itti dhiheenyaan hordofuu,
  2. Sagantaa walgahiiwwan boordii fi koree qopheessuu,
  3. Miseensonni boordii leenjii ijaarsa dandeettii bu’aa qabeessa fudhachuu isaanii mirkaneessuu.’’

11) Keewwata 39 (9): Hojii, Itti gaafatamummaa fi Aangoo Odiitaroota Baankichaa

Fooyya’iinsa taasifame- Keewwata xiqqaa 39(9) irratti fooyya’iinsi armaan gadii taasifamee jira.

‘’9. Waliigaltee baankii fi namoota baankicha waliin hidhata qaban gidduutti taasifamu ilaalchisee akkaataa barreeffama hundeeffamaa kana keewwata 23(3(h))tiin,  akkasumas bu’uura tumaalee seera daldalaa raawwatiinsa qabaniin murtoo kennuuf akka gargaaruuf haala waliigaltichaa, gosaa fi hanga kaffaltii raawwatamee, akkasumas haala walitti dhiheenya walitti bu’iinsa dantaaf sababa ta’een wal qabatee odeeffannoo gahaa dabaluun gabaasa barreeffamaa yaa’ii waliigalaatiif dhiyeessuu.’’

 

Dhuma irratti, akkaatuma olitti ibsameen fooyya’iinsi tokkoon tokkoon keewwattootaa irratti taasifame akkuma jirutti ta’ee, fooyya’iinsi godhame wal duraa duuba keewwatoota xiqqaa irratti jijjiirama hordofsiise ilaalchisee, yaa’insa yaadaa bifa eeggateenii fi walitti hidhata isaanii bifa ilaalcha keessa galcheen sirreeffamni barbaachisaan tartiiba isaanii irratti taasifamee jira. Bu’uuruma kanaan keewwattoonni 28, 29, 30 fi 37 fooyya’iinsi tartiibaa fi wal jalaa siquun duraa duuba keewwattoota xiqqaa irratti taasifamee jira.


ለኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ እና ምርጫ መስፈርት እና የጥቆማ ስነ-ስርዓትን ስለማሳወቅ

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንኮች አስተዳደር መመሪያ ቁጥር SBB/91/2024 አንቀጽ 9.3 መሰረት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ መስፈርት ምርጫ ከሚካሄድበት ጠቅላላ ጉባዔ አንድ ወር አስቀድሞ ለባለአክሲዮኖች መገለፅ እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ በመመሪያው አንቀጽ 9.4 መሰረት ደግሞ የጥቆማ ስነ-ስርዓቱም ከጉባዔው ቀን በፊት ለባለአክሲዮኖች መገለጽ አለበት፡፡ በመመሪያው እና በባንኩ ፖሊሲ እና ፕሮሲጀር መሰረት የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ከባንኩ ባለአክሲዮኖች፣ ሠራተኞች እና ነጻና ገለልተኛ ከሆኑ ዕጩዎች ውስጥ ከሚመረጡ ዳይሬክተሮች ይዋቀራል፡፡ በዚሁ አግባብ የባንኩ የቦርድ አባላት ጥቆማ እና ምርጫ መስፈርቶች እና የጥቆማ ስነ-ስርዓቱ እንደሚከተለው የቀረበ ሲሆን፣ ባለአክሲዮኖችም ታህሳስ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በሚያካሄደው 20ኛ የባለአክሲኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት አስፈላጊውን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና ብቁ የሆኑ የቦርድ አባላትን እንዲጠቁሙና እንዲመርጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

 

  1. የባንኩዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ ለመመረጥ ዕጩዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

       1.1 አጠቃላይ መስፈርት

የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ ለመመረጥ የሚጠቆም ሰው ተፈጻሚነት ባላቸው ሕጎች፣ በብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች እና በባንኩ የውስጥ ደንቦች ላይ የተቀመጡ የብቃት እና አግባብነት መመዘኛ መስፈርቶችን (fitness and propriety criteria) ማሟላት አለበት፡፡

      1.2 ዝርዝር መስፈርቶች

ማንኛውም በግልም ሆነ በህግ የሰውነት መብት የተሰጣቸውን ማህበራት ወይም ተቋማትን ወክሎ ለባንኩ የቦርድ አባልነት የሚጠቆም ባለአክሲዮን፣ እንዲሁም ሠራተኛ እና ነጻ እና ገለልተኛ የሆነ ዕጩ (Independent Directors) የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

ማንኛውም በግልም ሆነ በህግ የሰውነት መብት የተሰጣቸውን ማህበራት ወይም ተቋማትን ወክሎ ለባንኩ የቦርድ አባልነት የሚጠቆም ባለአክሲዮን፣ እንዲሁም ሠራተኛ እና ነጻ እና ገለልተኛ የሆነ ዕጩ (Independent Directors) የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

  1. ታማኝ፣ ሀቀኛ፣ ታታሪ፣ መልካም ስምና ዝና ያለው፤ በማጭበርበር፣ እምነት በማጉደል፣ ትክክለኛ ያልሆነ የሂሳብ መግለጫ በማቅረብ እና ተፈፃሚነት ባለው ህግ መሠረት ለቦርድ አባልነት ብቁ በማያደርግ ተመሳሳይ ወንጀል ጥፋተኝነቱ ያልተረጋገጠ፣
  2. በኪሳራ ምክንያት ንብረቱ ለዕዳ ማቻቻያነት ያልዋለ፣ የባንክ ብድር ባለመክፈሉ ምክንያት ንብረቱ በሐራጅ ያልተሸጠ፤ የሚመራው ወይም ዳይረክተር የሆነበት ድርጅት ከገንዘብ ተቋማት የተበደረውን ገንዘብ ባለመክፈሉ ብድሩ ወደ ጤናማ ያልሆነ የብድር ደረጃ ያልገባበት፣
  3. በቂ ስንቅ/ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ሰጥቶ ሂሳቡ ያልተዘጋበት፣ እንዲሁም ግብር ባለመክፈል ተከሶ ጥፋተኛ ያልተባለ፣
  4. ኃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት የሚያስፈልገውን በቂ ጊዜ ያለው፣
  5. የራሱን ሃሳብ በነፃነት የሚያራምድ እና የጥቅም ግጭት ሊያስነሱ የሚችሉ ነገሮችን የሚያስወግድ፣
  6. ከአራት በላይ በሆኑ ተቋማት ውስጥ በቦርድ ዳይሬክተርነት እየሰራ ያልሆነ፣ እና በሌላ የፋይናንስ ተቋም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ወይም ሰራተኛ ያልሆነ፣
  7. ዕድሜው ከ30 ዓመት ያላነሰ ከ70 ዓመት ያልበለጠ፣

1.3.ከባንኩ ባለአክሲዮኖች  ከባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎች እና ሠራተኞች ውስጥ ለሚጠቆሙ ዕጩዎች ተጨማሪ መስፈርቶች

ከላይ በተ.ቁ 1.1 እና 1.2 ስር ከተቀመጡት በተጨማሪ ባለአክሲዮን ወይም ሠራተኛ የሆነ ዕጩ፡-

  1. ከታወቀ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ቢያንስ የመጀመሪያ ድግሪ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ ያለው እና ለሥራው ተፈላጊነት ባለው የሙያ ዘርፍ (በባንኪንግ ወይም በፋይናነስ፣ በአደጋ ስጋት(ሪስክ) አስተዳደር፣ በሂሳብ አያያዝ፣ በንግድ ሥራ አስተዳደር፣ በኢኮኖሚክስ፣ በሕግ፣ በኦዲት ስራ፣ በመረጃ ቴክኖሎጂ፣ በኢንቨስትመንት አስተዳደር፣ በዘላቂነት /Sustainability/ እና በተዛማጅ የሙያ ዘርፍ ቢያንስ ከሰባት (7) ዓመታት ያላነሰ የሥራ ልምድ ያለው፣ እና
  2. ምርጫው ከሚካሄድበት ጉባዔ አስቀድሞ ባሉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት በባንኩ ባለአክሲዮንነት ተመዝግቦ የቆየ መሆን አለበት፡፡

1.4. ነጻና ገለልተኛ የሆኑ ዕጩ ዳይሬክተሮች

በብሔራዊ ባንክ የባንኮች አስተዳደር መመሪያ መሰረት ስራ ላይ ያለው ቦርድ በመመሪያው አንቀጽ 2.9፣ እንዲሁም በመመሪያ ቁጥር SBB/89/2024 አንቀጽ 2.8 እና 5.1.2 ስር በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት ነጻና ገለልተኛ የሆኑ የቦርድ ዕጩዎችን በመመልመል ዝርዝራቸውን ለጊዜያዊ የጥቆማ እና አስመራጭ ኮሚቴ የሚያስረክብ ሲሆን ኮሚቴው ደግሞ ዝርዝሩን ለጉባዔው አቅርቦ የዳይሬክተሮቹ ምርጫ ይከናወናል፡፡ በዜግነት ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ሰው የባንኩ ነጻና ገለልተኛ ዳይሬክተር ሆኖ መመረጥ ይችላል፡፡

  1. የቦርድአባላት ጥቆማ ስነ-ስርዓት
    • ጊዜያዊኮሚቴ ማቋቋም

የቦርድ አባላት ምርጫ በሚካሄድበት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የመጀመሪያ አጀንዳ የሚሆነው የጥቆማ እና ምርጫ ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት ሂደቱን የሚመራ እና የሚያስተባብር ጊዜያዊ የቦርድ አባላት የጥቆማ እና አስመራጭ ኮሚቴን ማቋቋም ነው፡፡ ኮሚቴው የሚቋቋመው በብሔራዊ ባንክ መመሪያ ውስጥ በተቀመጠው አግባብ የኮሚቴ አባላቱን በጉባዔው በመምረጥ ይሆናል፡፡

  • የጥቆማስነ-ስርዓት

ከቦርድ አባላት የጥቆማ ሂደት እና ስነ-ስርዓት ጋር ተያይዞ የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ከግንዛቤ ሊወሰዱ ይገባል፡፡

  1. የቦርድ አባላቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች ተጠቁመው በእነዚሁ ባለአክሲዮኖች የሚመረጡ፤ በሁሉም ባለአክሲዮኖች ተጠቁመው በሁሉም ባለአክሲዮኖች የሚመረጡ፤ እንዲሁም በቦርዱ ተጠቁመው በሁሉም ባለአክሲዮኖች የሚመረጡ ነጻና ገለልተኛ የሆኑ ዕጩ ዳይሬክተሮች ይሆናሉ፣
  2. የነፃና ገለልተኛ እጩዎች ጥቆማን ሳይጨምር የሁሉም ዳይሬክተሮች ጥቆማ እና ምርጫ የሚካሄደው በጉባዔው ዕለት ነው፣
  3. የባንኩ ባለአክሲዮን እራሱን ወይም ሌሎች ባለአክሲዮኖችንና ሠራተኞችን ለቦርድ አባል ዕጩነት መጠቆም ይችላል፣
  4. የጊዜያዊ የቦርድ አባላት ጥቆማ እና አስመራጭ ኮሚቴ አባል ለቦርድ አባልነት መጠቆም አይችልም፤
  5. ጥቆማ ሲሰጥ ቦርዱ በቂ የፆታ፤ የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ ስብጥር ሊኖረው የሚገባ መሆኑ ከግንዛቤ መወሰድ አለበት፤
  6. ባለአክሲዮኖች የሚጠቁሙትን ግለሰብ ወይም የሕግ ሰውነት ያለው ድርጅትን ወክሎ የሚጠቆም የተፈጥሮ ሰውን የትምህርት ደረጃ፣ የስራ ልምድ እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ በቂና ትክክለኛ መረጃን መስጠት አለባቸው፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • ከላይ በወንድ ጾታ የተገለፀው ለሴት ፆታም ያገለግላል፣
  • ከአጠቃላይ የቦርድ አባላት ውስጥ ቢያንስ ሁለቱ (2) ሴቶች መሆን አለባቸው፡፡

Waamicha Yaa’ii Ariifachiisaa 11ffaa Abbootii Aksiyoonaa fi Yaa’ii Waliigalaa Idilee 20ffaa Baankii Hojii Gamtaa Oromiyaa (W.A)

Bu’uura Seera Daldalaa R.F.D.I keewwata 366(1), 367(1) fi keewwata 370 akkasumas Barreeffama Hundeeffamaa baankichaa keewwata 17(1) fi 18(1)tti Baankiin Hojii Gamtaa Oromiyaa(W.A) Yaa’ii Ariifachiisaa 11ffaa Abbootii Aksiyoonaa fi Yaa’ii Waliigalaa Idilee 20ffaa Sanbata Mudde 19, 2017 ganama sa’aatii 2 irraa kaasee magaalaa Adaamaa, Galma Abbaa Gadaatti ni teessisa. Kanaafuu, kabajamtootni abbootii aksiyoonaa waldaa aksiyoonichaa, yookaan bakka bu’ootni seera qabeeyyiin, iddoo guyyaa fi sa’aatii eerametti akka nuuf argamtan Boordiin Daayrektarootaa Baankichaa waamicha isiniif godheera

 

  1. Ragaalee ijoo waldicha ilaalan:

Maqaa waldichaa: Baankii Hojii Gamtaa Oromiyaa(W.A)

Akaakuu waldichaa: Waldaa aksiyoonaa hojii baankii irratti argamu,

Teessoo waajjira muummee waldaa aksiyoonichaa: Finfinnee, Kutaa Magaalaa Boolee, Aanaa 02, Lakk. Manaa Haaraa,

Marsariitii Baankichaa: https://www.coopbankoromia.com.et

Lakk. Galmee Waldaa Aksiyoonichaa: KK/AA/3/0001918/2004

Maallaqni Waldaa Aksiyoonichaa /Kaappitaala/ waliigalaan Mallattaa’e: 12,800,000,000.00

Maallaqa Waldaa Aksiyoonichaa /kaappitaala/ waliigalaan kaffalame: 11,253,744,600.00

  1. Ajandaawwan Yaa’ii Waliigalaa Ariifachiisaa 11ffaa

2.1 Barreeffama Hundeeffamaa baankichaa fooyyessuuf yaada murtoof dhiyaate irratti mari’achuun murteessuu,

  1. Ajandaawwan Yaa’ii Waliigalaa Idilee Waggaa 20ffaa

3.1 ALA Mudde 1/2023 hanga Sadaasa 30/2024tti dabarsa aksiyoonaa taasifamanii fi baay’ina abbootii aksiyoonaa raggaasisuu,

3.2 Imaammataa fi hojimaata raawwii eerinsaa fi filannoo miseensota boordii daayrektarootaa mari’atanii raggaasisuu,

3.3 Koree eerinsaa fi filannoo miseensota boordii daayrektarootaa yeroof tajaajilu filuu,

3.4 Gabaasa Waggaa Boordii Daayrektarootaa kan bara 2023/24 ALA dhaggeeffachuu fi mari’atanii murteessuu,

3.5 Gabaasa Waggaa Odiitaroota Alaa baankichaa kan bara 2023/24 ALA dhaggeeffachuu fi mari’atanii murteessuu,

3.6 Odiitaroota keessaa bara 2023/24 ALA muuduu fi kaffaltii isaanii murteessuu,

3.7 Filannoo miseensota boordii daayreektarootaa taasisuu.

3.8 Ramaddii bu’aa qulqulluu fi kaffaltii bara herreegaa ALA 2023/24 irratti mari’atanii murteessuu,

3.9 Kaffaltii waggaa Boordii Daayrektarootaa ALA bara 2023/24 fi durgoo ji’aa bara 2024/25 murteessuu,

  1. Hubachiisa

4.1. Abbootiin aksiyoonaa yaa’ii kana irratti argamuu hin dandeenye, bakka bu’ootni isaanii ragaa bakka bu’iinsaa qaama mootummaa aangoo qabuun mirkanaa’ee kenname, orijinaalaa fi koppii qabachuun ykn akkaataa Seera Daldalaa keewwata 377n yaa’iin adeemsifamuun guyyaa sadii(3) dura Waajjira Muummee baankichaa, magaalaa Finfinnee Daandii Afriikaa, naannoo maqa Imbaasii  Ruwaandaatti argamu darbii 7ffaa Kutaa Bulchiinsa Aksiyoonaatti ykn damee baankichaa isaanitti dhihoo jirutti qaamaan argamuun, unka bakka bu’iinsaa dhimma kanaaf baankichaan qophaa’e guutanii mallatteessuun bakka bu’aa muuduu fi bakka bu’aanis ragaa bakka bu’iinsaa qabachuun yaa’ii irratti hirmaachuu fi sagalee kennuu kan dandeessan ta’uu kabajaan ibsina. Haata’u malee, abbaan aksiyoonaa tokko yaa’ii waliigalaa waldichaaf dandeettii kamiinuu kan bakka buusuu danda’u nama tokko qofa ta’uu ni beeksisna.

4.2. Abbootiin aksiyoonaa waldaa aksiyoonichaa ykn bakka bu’ootni seera qabeeyyiin, yaa’icha irratti hirmaachuuf yommuu dhufan, lammummaan Itoophiyaa ta’uu isaanii kan ibsu Waraqaa Eenyummaa ykn Paaspoortii ykn Hayyama Konkolaachisummaa, orijinaalaa fi koppii isaa qabachuun yaa’icha irratti hirmaachuu ni danda’u. Akkasumas, abbootii aksiyoonaa dhalattoota Itoophiyaa lammummaa biyya alaa qaban, dhalootaan Itoophiyaa ta’uu isaanii kan mirkaneessu, waraqaa eenyummaa/kaardii keelloo/ yeroon isaa irra hin dabarre, qabatanii dhiyaachuu kan qaban ta’uu kabajaan ibsina.

4.3 Bakka bu’aan dhaabbata, (Waldaa Hojii Gamtaa ykn dhaabbata biroo) bakka bu’ee, dhiyaatu, hojii gaggeessaaa dhaabbatichaa / waldichaa ta’uu ragaa mirkaneessu qabatee dhiyaachuu ykn uunka bakka bu’iinsaa baankichaan, bakka bu’iinsa kenname qabatee dhiyaachuu kan qabu ta’uu kabajaan ibsina.

4.4 Akkaataa qajeelfama bulchiinsa baankolee Baankii Biyyoolessaa Itoophiyaa Lakk. SBB/91/2024 keewwata 20(3)n miseensotni boordii baankichaa fi hojjattootni baankichaa abbootii aksiyoonaa bakka bu’uun yaa’icha irratti hirmaachuu hin danda’an.

4.5 Hangi bakka bu’iinsaa bakka bu’ootni fudhatan, kan isaanii dabalatee kaappitaala baankichaa mallattaa’e dhibbentaa kudhan caaluu hin qabu.

Boordii DaayrektarootaaBaankii Hojii Gamtaa Oromiyaa (W.A)


የጠቅላላ ጉባኤ ቀን ለውጥ ማስታወቂያ!

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ የባለአክሲዮኖች 20ኛ መደበኛ እና 11ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ለታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ተጠርቶ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የጉባኤው ቀን ለአንድ ሳምንት ተራዝሞ ወደ ታህሳስ 19 ቀን 2017 ዓ.ም. የተቀየረ መሆኑን ከታላቅ ይቅርታ ጋር እናሳውቃለን።


Beeksisa Jijjiirraa Guyyaa Yaa'ii Waliigalaa!

Yaa’iin Waliigalaa Idilee 20ffaa fi Yaa’ii Ariifachiisaa 11ffaa  Abbootii Aksiyoonaa Baankii Hojii Gamtaa Oromiyaa W.A, Mudde 12 bara 2017tti waamamee turuunsaa ni yaadatama. Haa ta'u malee, sababa humnaa oliitiin, guyyaan yaa'ichaa torban tokkoof dheeratee, Mudde 19 bara 2017tti jijjiiramuusaa dhiifama guddaa waliin isin beeksifna.

 


Abbootii Aksiyoonaa Baankii Hojii Gamtaa Oromiyaa(W.A) naamusaa fi ulaagaalee eeriinsaa fi filannoo miseensota boordii beeksisuu

Akka maxxansaalee gaazexaa Addis Zamanii fi Ripportaraa Sadaasa 8, bara 2017 irratti Ibsametti, akkaataa qajeelfama bulchiinsa baankolee Baankii Biyyoolessaa Itoophiyaa Lakk. SBB/91/2024 Keewwata 9.3tti ulaagaalee eerinsaa fi filannoo miseensota boordii yaa’ii waliigalaa filannoon irratti taasifamu ji’a tokkoon dura abbootii aksiyoonaaf akka ibsamuu qabu ajaja/tuma. Akkaataa qajeelfamichaa keewwata 9.4tti ammo naamusni eeriinsaas guyyaa yaa’ichaatiin dura abbootii aksiyoonaaf ibsamuu qaba. Akkaataa qajeelfama kanaan, imaammataa fi pirosiijara baankichaatiin, boordiin daayrektarootaa baankichaa, abbootii aksiyoonaa baankichaa, hojjattootaa fi kaadhimamtoota bilisaafi walitti dhiheenya hin qabne keessaa daayrektaroota filataman irraa hundaa’a. Haaluma kanaan naamusnii fi ulaagaaleen eerinsaa fi filannoon miseensota boordii baankichaa akka armaan gaditti kan dhiyaate yommuu ta’u, abbootiin aksiyoonaa yaa’ii waliigalaa idilee waggaa 20ffaa Mudde 12, 2017 taa’amu irratti argamuun, miseensota boordii ulaagaalee barbaachisoo guutanii fi gahumsa qaban akka eeranii fi filatan waamicha keenya dhiheessina.

  1. Miseensa boordii daayrektarootaa baankichaa ta’uun filatamuuf ulaagaaleen kaadhimamtoonni guutuu qaban:

1.1. Ulaagaa Waliigalaa

Namni miseensa boordii baankichaa ta’ee filamuuf eeramu, seerota raawwatamoo ta’an, qajeelfamoota Baankii Biyyoolessaa fi damboota keessoo baankichaa irratti ulaagaalee madaallii gahumsaa fi fudhatamaa kaa’aman, (fitness and propriety criteria) guutuu qaba.

1.2. Ulaagaalee bal’inaan

Abbaan aksiyoonaa dhuunfaattis ta’ee waldaalee yookaan dhaabbilee qaamni seerummaa kennameef bakka bu’ee miseensummaa boordii baankichaatiif abbaan aksiyoonaa eeramu, akkasumas hojjataa fi kaadhimamaan bilisaa fi walitti dhufeenya hin qabne, (Independent Directors) ulaagaalee kana guutuu qaba.

  1. Amanamaa, kan haqaan bulu, hojii irratti cimaa, maqaa gaarii kan qabu, malaa maluun, amanamuu diduun, ibsa herreegaa dharaa dhiyeessuunii fi akkaataa seera raawwatamuu danda’uuni fi yakka miseensummaa boordiif gahumsa akka hin qabaanne taasisuun, balleessaadha jedhamee kan itti hin muramne.
  2. Sababa kisaaraatiin qabeenyi isaa idaa bakka buusuuf kan jalaa hin fudhatamne, liqii baankii kaffaluu dadhabuun kan qabeenyi jalaa hin gurguramne, dhaabbanni inni hoogganu, yookaan kan daayrektarummaan gaggeessu liqii dhaabbilee faaynaansii irraa liqeeffate kaffaluu dhabuun liqiin isaa gara sadarkaa liqii hin milkoofnetti kan duraa hin ceene.
  3. Galaan/maallaqni gahaan odoo hin jiraatiin cheekii kennee herreegni kan jalaa hin cufamne akkasumas gibira kaffaluu diduun himatamee balleessaa ta’uun kan itti hin mirkanoofne.
  4. Ittigaafatama isaa haala gaariin bahuuf yeroo gahaa kan qabu.
  5. Yaada ofii bilisaan kan ibsatu fi dhimmoota walitti bu’iinsa faayidaa uumuu danda’an kan maqsu.
  6. Dhaabbilee lakkoofsaan afurii ol ta’aan keessatti daayrektarummaa boordiin kan hojjachaa hin jirree fi dhaaba faaynaansii kan biraa keessatti miseensummaa boordiin yookaan hojjataa ta’uun kan tajaajilaa hin jirre.
  7. Umuriin isaa waggaa 30 gadi kan hin taane waggaa70 kan hin caalle.

1.3.Abbootii aksiyoonaa baankichaa, Hojii Raawwachiisaa Olaanaa baankii fi itti aantota Hojii Raawwachiistota Olaanoo baankichaa fi hojjattoota keessaa kan kaadhimamtoota eeramaniif ulaagaalee dabalataa kaa’aman

Olitti Lakk. 1.1 fi 1.2 jalatti kan kaa’amanitti dabalataan kaadhimamaan abbaa aksiyoonaa yookaan hojjataa ta’e tokko:

  1. Sadarkaa barnootaa dhaabbata barumsaa beekamaa irraa yoo xiqqaate digrii jalqabaa fi kan isa gitu kan qabuu fi toora ogummaa hojichaaf barbaachisummaa qabu(baankii yookaan faaynaansii, bulchiinsa riiskii, qabiisa herregaa, bulchiinsa hojii daldalaa, Ikonomiksii, seera, hojii odiitii, teknoloojii odeeffannoo, bulchiinsa investimantii, sastenebilitii fi ogummaa wal fakkaatuun muuxannoo yoo xiqqaate waggaa 7 gadi hin taane qabu, fi
  2. Yaa’ii filannoon irratti taasifamu dura waggoota lama baankichatti abbaa aksiyoonummaan kan galmaa’ee ture ta’uu qabaata.

1.4. Daayrektaroota kaadhimamoo bilisaa fi walitti dhufeenya hin qabne 

Akkaataa qajeelfama bulchiinsa baankolee, Baankii Biyyoolessaatti boordiin hojiirra jiru qajeelfama keewwata 2.9n akkasumas Lakk. qajeelfamaa SBB/89/2024 keewwata 2.8 fi 5.1.2 jalatti ulaagaalee tarreeffamaniin kaadhimamtoota boordii bilisaa fi walitti dhufeenya hin qabne adda baasuun tartiiba isaanii koree eerinsaa fi filachiistuu yeroodhaaf hundaa’eetti kan dabarsu yommuu ta’u, koreen ammo tartiiba kana yaa’iitti dhiheessee, filannoon daayrektarootaa ni taasifama. Namni lammummaan Itoophiyaa hin taane daayrektara bilisaa fi walitti dhufeenya hin qabne ta’ee filatamuu ni danda’a.

  1. Naamusa eeruu miseensota boordii

2.1. Koree yeroodhaaf hundeessuun

yaa’ii waliigalaa filannoon miseensota boordii irratti taasifamu irratti ajandaa jalqabaa kan ta’u, adeemsi eeruu fi filannoo otoo hin jalqabamin dura, adeemsa isaa kan gaggeessuu fi kan qindeessu koree eeruu fi filannoo miseensota boordii hundeessuudha. Koreen kan hundaa’u akkaataa qajeelfama Baankii Biyyoolessaa keessa taa’een miseensota koree yaa’ichaan filuun ta’a.

2.2. Naamusni eerinsaa

adeemsa eeruu fi naamusa miseensota boordii waliin walqabatee, qabxiileen ijoo armaan gadii ilaalcha keessa galuu qabaatu.

  1. Miseensonni boordii abbootii aksiyoonaa dhiibbaa uumuu hin dandeenyeen eeramanii, abbootii aksiyoonaa kanaan filataman, abbootii aksiyoonaa hundaan eeramanii abbootii aksiyoonaa hundaan kan filataman, akkasumas boordichaan eeramanii abbootii aksiyoonaa hundaan kan filataman kaadhimamtoonni daayrektaroota bilisaa fi walitti dhufeenya hin qabne ta’u.
  2. Eerinsa kaadhimamtoota bilisaa fi walitti dhufeenya hin qabne, otoo hin dabalatiin, eerinsii fi filannoon kan taasifamu gaafa yaa’ichaa ta’a.
  3. Abbaan aaksiyoonaa baankichaa, ofii isaa yookaan abbootii aksiyoonaa biroo fi hojjattoota kaadhimamummaa miseensummaa boordiif eeruu ni danda’a.
  4. Koreen eerinsaa fi filannoo miseensota boordii yeroodhaaf hundaa’u miseensummaa boordiif nama eeruu hin danda’u.
  5. Yommuu eerumsi taasifamu, boordichi saala, sadarkaa barumsaa fi muuxannoon hojii haala wal madaaluun wal keessa makamuu akka qabu ilaalcha keessa galchuu qabaata.
  6. Abbootiin aksiyoonaa sadarkaa barnootaa, muuxannoo hojii fi dhimmoota biraa nama dhuunfaa yookaan nama dhaabbata qaama seerummaa qabu bakka bu’uun eeran, kan ilaaluun ragaa sirrii fi gahaa ta’e kennuu qabu.

Hubachiisa

  • Olitti saala dhiiraatiin kan ibsame dubartiidhaafis ni tajaajila,
  • Miseensota boordii waliigalaa keessaa yoo xiqqaate lama dubartoota ta’uu qabu.

 


ለኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ እና ምርጫ መስፈርት እና የጥቆማ ስነ-ስርዓትን ስለማሳወቅ

ኅዳር 8፣ 2017 ዓ.ም በወጡት የአዲስ ዘመን እና ሪፖርተር ጋዜጣ እትሞች ላይ እንደተመለከተው፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንኮች አስተዳደር መመሪያ ቁጥር SBB/91/2024 አንቀጽ 9.3 መሰረት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ መስፈርት ምርጫ ከሚካሄድበት ጠቅላላ ጉባዔ አንድ ወር አስቀድሞ ለባለአክሲዮኖች መገለፅ እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ በመመሪያው አንቀጽ 9.4 መሰረት ደግሞ የጥቆማ ስነ-ስርዓቱም ከጉባዔው ቀን በፊት ለባለአክሲዮኖች መገለጽ አለበት፡፡ በመመሪያው እና በባንኩ ፖሊሲ እና ፕሮሲጀር መሰረት የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ከባንኩ ባለአክሲዮኖች፣ ሠራተኞች እና ነጻና ገለልተኛ ከሆኑ ዕጩዎች ውስጥ ከሚመረጡ ዳይሬክተሮች ይዋቀራል፡፡ በዚሁ አግባብ የባንኩ የቦርድ አባላት ጥቆማ እና ምርጫ መስፈርቶች እና የጥቆማ ስነ-ስርዓቱ እንደሚከተለው የቀረበ ሲሆን ባለአክሲዮኖችም ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በሚያካሄደው 20ኛ የባለአክሲኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት አስፈላጊውን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና ብቁ የሆኑ የቦርድ አባላትን እንዲጠቁሙና እንዲመርጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

  1. የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ ለመመረጥ ዕጩዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

       1.1 አጠቃላይ መስፈርት

የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ ለመመረጥ የሚጠቆም ሰው ተፈጻሚነት ባላቸው ሕጎች፣ በብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች እና በባንኩ የውስጥ ደንቦች ላይ የተቀመጡ የብቃት እና አግባብነት መመዘኛ መስፈርቶችን (fitness and propriety criteria) ማሟላት አለበት፡፡

      1.2 ዝርዝር መስፈርቶች

ማንኛውም በግልም ሆነ በህግ የሰውነት መብት የተሰጣቸውን ማህበራት ወይም ተቋማትን ወክሎ ለባንኩ የቦርድ አባልነት የሚጠቆም ባለአክሲዮን፣ እንዲሁም ሠራተኛ እና ነጻ እና ገለልተኛ የሆነ ዕጩ (Independent Directors) የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

ማንኛውም በግልም ሆነ በህግ የሰውነት መብት የተሰጣቸውን ማህበራት ወይም ተቋማትን ወክሎ ለባንኩ የቦርድ አባልነት የሚጠቆም ባለአክሲዮን፣ እንዲሁም ሠራተኛ እና ነጻ እና ገለልተኛ የሆነ ዕጩ (Independent Directors) የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

  1. ታማኝ፣ ሀቀኛ፣ ታታሪ፣ መልካም ስምና ዝና ያለው፤ በማጭበርበር፣ እምነት በማጉደል፣ ትክክለኛ ያልሆነ የሂሳብ መግለጫ በማቅረብ እና ተፈፃሚነት ባለው ህግ መሠረት ለቦርድ አባልነት ብቁ በማያደርግ ተመሳሳይ ወንጀል ጥፋተኝነቱ ያልተረጋገጠ፣
  2. በኪሳራ ምክንያት ንብረቱ ለዕዳ ማቻቻያነት ያልዋለ፣ የባንክ ብድር ባለመክፈሉ ምክንያት ንብረቱ በሐራጅ ያልተሸጠ፤ የሚመራው ወይም ዳይረክተር የሆነበት ድርጅት ከገንዘብ ተቋማት የተበደረውን ገንዘብ ባለመክፈሉ ብድሩ ወደ ጤናማ ያልሆነ የብድር ደረጃ ያልገባበት፣
  3. በቂ ስንቅ/ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ሰጥቶ ሂሳቡ ያልተዘጋበት፣ እንዲሁም ግብር ባለመክፈል ተከሶ ጥፋተኛ ያልተባለ፣
  4. ኃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት የሚያስፈልገውን በቂ ጊዜ ያለው፣
  5. የራሱን ሃሳብ በነፃነት የሚያራምድ እና የጥቅም ግጭት ሊያስነሱ የሚችሉ ነገሮችን የሚያስወግድ፣
  6. ከአራት በላይ በሆኑ ተቋማት ውስጥ በቦርድ ዳይሬክተርነት እየሰራ ያልሆነ፣ እና በሌላ የፋይናንስ ተቋም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ወይም ሰራተኛ ያልሆነ፣
  7. ዕድሜው ከ30 ዓመት ያላነሰ ከ70 ዓመት ያልበለጠ፣

1.3.ከባንኩ ባለአክሲዮኖች ከባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎች እና ሠራተኞች ውስጥ ለሚጠቆሙ ዕጩዎች ተጨማሪ መስፈርቶች

ከላይ በተ.ቁ 1.1 እና 1.2 ስር ከተቀመጡት በተጨማሪ ባለአክሲዮን ወይም ሠራተኛ የሆነ ዕጩ፡-

  1. ከታወቀ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ቢያንስ የመጀመሪያ ድግሪ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ ያለው እና ለሥራው ተፈላጊነት ባለው የሙያ ዘርፍ (በባንኪንግ ወይም በፋይናነስ፣ በአደጋ ስጋት(ሪስክ) አስተዳደር፣ በሂሳብ አያያዝ፣ በንግድ ሥራ አስተዳደር፣ በኢኮኖሚክስ፣ በሕግ፣ በኦዲት ስራ፣ በመረጃ ቴክኖሎጂ፣ በኢንቨስትመንት አስተዳደር፣ በዘላቂነት /Sustainability/ እና በተዛማጅ የሙያ ዘርፍ ቢያንስ ከሰባት (7) ዓመታት ያላነሰ የሥራ ልምድ ያለው፣ እና
  2. ምርጫው ከሚካሄድበት ጉባዔ አስቀድሞ ባሉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት በባንኩ ባለአክሲዮንነት ተመዝግቦ የቆየ መሆን አለበት፡፡

1.4. ነጻና ገለልተኛ የሆኑ ዕጩ ዳይሬክተሮች

በብሔራዊ ባንክ የባንኮች አስተዳደር መመሪያ መሰረት ስራ ላይ ያለው ቦርድ በመመሪያው አንቀጽ 2.9፣ እንዲሁም በመመሪያ ቁጥር SBB/89/2024 አንቀጽ 2.8 እና 5.1.2 ስር በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት ነጻና ገለልተኛ የሆኑ የቦርድ ዕጩዎችን በመመልመል ዝርዝራቸውን ለጊዜያዊ የጥቆማ እና አስመራጭ ኮሚቴ የሚያስረክብ ሲሆን ኮሚቴው ደግሞ ዝርዝሩን ለጉባዔው አቅርቦ የዳይሬክተሮቹ ምርጫ ይከናወናል፡፡ በዜግነት ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ሰው የባንኩ ነጻና ገለልተኛ ዳይሬክተር ሆኖ መመረጥ ይችላል፡፡

  1. የቦርድ አባላት ጥቆማ ስነ-ስርዓት
    • ጊዜያዊ ኮሚቴ ማቋቋም

የቦርድ አባላት ምርጫ በሚካሄድበት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የመጀመሪያ አጀንዳ የሚሆነው የጥቆማ እና ምርጫ ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት ሂደቱን የሚመራ እና የሚያስተባብር ጊዜያዊ የቦርድ አባላት የጥቆማ እና አስመራጭ ኮሚቴን ማቋቋም ነው፡፡ ኮሚቴው የሚቋቋመው በብሔራዊ ባንክ መመሪያ ውስጥ በተቀመጠው አግባብ የኮሚቴ አባላቱን በጉባዔው በመምረጥ ይሆናል፡፡

  • የጥቆማ ስነ-ስርዓት

ከቦርድ አባላት የጥቆማ ሂደት እና ስነ-ስርዓት ጋር ተያይዞ የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ከግንዛቤ ሊወሰዱ ይገባል፡፡

  1. የቦርድ አባላቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች ተጠቁመው በእነዚሁ ባለአክሲዮኖች የሚመረጡ፤ በሁሉም ባለአክሲዮኖች ተጠቁመው በሁሉም ባለአክሲዮኖች የሚመረጡ፤ እንዲሁም በቦርዱ ተጠቁመው በሁሉም ባለአክሲዮኖች የሚመረጡ ነጻና ገለልተኛ የሆኑ ዕጩ ዳይሬክተሮች ይሆናሉ፣
  2. የነፃና ገለልተኛ እጩዎች ጥቆማን ሳይጨምር የሁሉም ዳይሬክተሮች ጥቆማ እና ምርጫ የሚካሄደው በጉባዔው ዕለት ነው፣
  3. የባንኩ ባለአክሲዮን እራሱን ወይም ሌሎች ባለአክሲዮኖችንና ሠራተኞችን ለቦርድ አባል ዕጩነት መጠቆም ይችላል፣
  4. የጊዜያዊ የቦርድ አባላት ጥቆማ እና አስመራጭ ኮሚቴ አባል ለቦርድ አባልነት መጠቆም አይችልም፤
  5. ጥቆማ ሲሰጥ ቦርዱ በቂ የፆታ፤ የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ ስብጥር ሊኖረው የሚገባ መሆኑ ከግንዛቤ መወሰድ አለበት፤
  6. ባለአክሲዮኖች የሚጠቁሙትን ግለሰብ ወይም የሕግ ሰውነት ያለው ድርጅትን ወክሎ የሚጠቆም የተፈጥሮ ሰውን የትምህርት ደረጃ፣ የስራ ልምድ እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ በቂና ትክክለኛ መረጃን መስጠት አለባቸው፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • ከላይ በወንድ ጾታ የተገለፀው ለሴት ፆታም ያገለግላል፣
  • ከአጠቃላይ የቦርድ አባላት ውስጥ ቢያንስ ሁለቱ (2) ሴቶች መሆን አለባቸው፡፡