የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ 18ኛ የባለ አክሲዮኖች ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 10ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዳማ ከተማ፡ አባገዳ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም ባለ አክሲዮኖች በተጠቀሰው ቦታ ቀንና ሰዓት በመገኘት የጉባኤው ተሳታፊ እንድትሆኑ የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ይጋብዛል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ባለ አክሲዮኖች ወይም ተወካዮች በጉባኤው ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው መሆኑን ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያሳይ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ዋናውን እና አንድ ኮፒ መያዝ ያለባቸው መሆኑን፤
- በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለ አክሲዮኖች በንግድ ሕጉ አንቀፅ 377 (1) መሠረት አዲስ አበባ ቦሌ መንገድ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ፣ ራንግ ህንፃ፣ 9ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የባንኩ አክሲዮን አስተዳደር ክፍል ወይም በአቅራቢያቸው በሚገኘው የባንኩ ቅርንጫፍ በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን የውክልና መስጫ ቅጽ በመሙላት በተወካያቸው ተገኘተው መሳተፍ እና ድምፅ መስጠት የሚችሉ መሆኑን፤
- ድርጅትን (የኅብረት ሥራ ማህበርን ወይም ሌላ ድርጅትን) ወክሎ የሚቀርብ ተወካይ የድርጅቱ/የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዞ መቅረብ ያለበት መሆኑ፤ አለዚያም የባንኩ የውክልና መስጫ ቅጽ መሠረት ውክልና የተሰጠው መሆኑን፤
- ከላይ በተራ ቁጥር 2 እና 3 ሥር ከተመለከቱት ውጭ በውክልና በስብሰባው ላይ ለመገኘት የሚፈልጉ ካሉ ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው የመንግስት አካል የተሰጠ በጉባኤው ለመሳተፍ እና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ይዘው መምጣት ያለባቸው መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
- የጉባኤውን አጀንዳዎች በተመለከተ፡- የህዳር 11 ፤2015 የሪፖርተር እና አዲስ ዘመን ጋዜጣ እትምችን መመልከት ይቻላል፡፡
ለበለጠ መረጃ 0115150229 ስልክ ቁጥሮችን ይጠቀሙ፡፡
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ
የዳይሬክተሮች ቦርድ