ለኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

የባንክ ሥራ አዋጅ ቁጥር 592/2000፣ የኢትዮዽያን ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/62/2015 እና SBB/54/2012 እንዲሁም የባንኩን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የጥቆማና የምርጫ ማስፈጸሚያ የውስጥ መመሪያ መሠረት በማድረግ በቀጣይ ባንኩን በቦርድ አባልነት የሚመሩ አባላትን ለማስመረጥ ኅዳር  16 ቀን 2010 ዓ.ም.  በተካሄደው የባለአክሲዮኖች 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የተቋቋመው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

በዚሁ መሠረት ባለአክሲዮኖች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ  እጩ የቦርድ አባላትን እንድትጠቁሙ  አስመራጭ ኮሚቴው በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

 1. የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ባለአክሲዮን የሆነ/ች እና ቢመረጥ/ብትመረጥ በዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ/ች፣
 2. ኢትዮዽያዊ ዜጋ የሆነ/ች እንዲሁም ዕድሜው/ዋ 30 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
 3. የትምህርት ደረጃ፣

ሀ. ቢያንስ 75% የሚሆኑት የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ ከታወቀ የትምህርት ተቋም ያላቸው፣

ለ. የቀሩት 25% ቢያንስ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ ያላቸው መሆን አለባቸው፣

 1. የሥራ ልምድ፡- በባንክ ሥራ፣ በፋይናንስ፣ በአካውንቲንግ፣ በሕግ፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን/ሊደርሺፕ፣ በኦዲቲንግ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣በኢንቨስትመንት ማኔጅመንት፣ በሕብረት ሥራ አመራር፣ በማኀበራዊና በጐ አድራጐት ሥራዎች፣ በብዙኃን ማኅበራት እና ሌሎች ተዛማጅነት ባላቸው ሙያዎች ላይ በቂ የሥራ ልምድ ያለው/ላት መሆን አለበት/ባት፣
 2. የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ/ች፣ የባንኩ ወይም የሌላ ባንክ ተቀጣሪ ሠራተኛ ያልሆነ/ች፣
 3. የማንኛውም የፋይናንስ ተቋም የዳይሮክተሮች ቦርድ አባል ወይም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ያልሆነ/ች፣
 4. ተጠቋሚው የሕግ ሰውነት ያለው ድርጅት ከሆነ ድርጅቱን የሚወክል የተፈጥሮ ሰው ማንነት መገለጽ ያለበት ሲሆን ተጠቋሚው የሚወክለውን ድርጅት 10% እና ከዚያ በላይ የባለቤትነት ድርሻ የያዘ መሆን የለበትም/የለባትም፣
 5. በኢትዮዽያና ከኢትዮዽያ ውጭ የዕምነት ማጉደል ወይም የማጭበርበር ተግባር ያልፈጸመ/ች፣ ከመንግሥት አካላት መረጃ ያልደበቀ/ች፣ ለፋይናንሻል ተቋማትና ለተቆጣጣሪ አካል ሐሰተኛ መረጃ ያልሰጠ/ች፣ የሥነ-ምግባር ደንቦችን ባለማክበር የሥነ-ሥርዓት እርምጃ ያልተወሰደበት/ባት፣በሙስና ወንጀል ተከሶ/ሳ ያልተፈረደበት/ባት፣ ከመምረጥና መመረጥ መብት ያልተገደበ/ች፣
 6. በኢትዮዽያና ከኢትዮጵያ ውጭ በማናቸውም በፈረሰ ባንክ ዳይሬክተር፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይም ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚ ያልነበረ/ች፣ ወይም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በባንኩ ሥራ አመራር ላይ ያልተሳተፈ/ች፣
 7. የፋይናንሻል ጤናማነትን መስፈርት የሚያሟላ/የምታሟላ፤ ማለትም በኢትዮዽያና ከኢትዮዽያ ውጭ በኪሳራ ላይ ያልሆነ/ች፣ የታክስና የባንክ ግዴታዎችን የተወጣ/ች፣የባንክ ብድር ባለመክፈሉ/ሏ ምክንያት ንብረቱ/ቷ ያልተሸጠ፣ ከማንኛውም የፋይናንስ ተቋም የተወሰደ ጤናማ ያልሆነ ብድር የሌለበት/ባት፣ በደረቅ ቼክ ምክንያት የባንክ ሂሳብ  ያልተዘጋበት/ባት፣
 8. ከሚጠቆሙት እጩዎች መካከል 1/3ኛው ተፅዕኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች (ከባንኩ ጠቅላላ የተፈረመ ካፒታል 2% በታች ባላቸው) ብቻ ከተጠቆሙት እጩዎች ውስጥ ይወሰዳሉ፣
 9. ቀሪዎቹ 2/3ኛ እጩዎች ሁሉም ባለአክሲዮኖች ከሚጠቁሙት ውስጥ ይወሰዳሉ፣
 10. አንድ ባለአክሲዮን መጠቆም የሚችለው አንድ ዕጩ ብቻ ነው፡፡ ባለአክሲዮኑ ከአንድ እጩ በላይ ከጠቆመ  ጥቆማው ውድቅ ይሆናል፣
 11. ማንኛውም ባለአክሲዮን ራሱን ወይም የሕግ ሰውነት ያለውን ድርጅት በመወከል ከተከታታይ ስድስት ዓመታት በላይ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ የቦርድ አባል ሆኖ መመረጥ አይችልም፣
 12. ራሱን ወይም የሕግ ሰውነት ያለውን ድርጅት በመወከል ለስድስት ተከታታይ ዓመታት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል በመሆን ያገለገለ ባለአክሲዮን እንደገና ለቦርድ አባልነት መጠቆም የሚቻለው ከቦርድ አባልነቱ/ቷ ከተነሳ/ች ከተከታታይ ስድስት ዓመታት በኋላ ነው፣
 13. ከላይ በተራ ቁጥር 14 እና 15 የተገለጸው ቢኖርም፣ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ የዳይሬክተሮች ቦርድ ቀጣይነትን ለማረጋገጥ አስፈላጊ ነው ብሎ ካመነበት ከነባር ቦርድ አባላት በተከታታይ ለስድስት ዓመታት ያገለገሉትን ለአንድ ተጨማሪ የሥራ ዘመን (ለሶስት ዓመት) ብቻ እንደገና ለቦርድ አባልነት ሊመርጥ የሚችል ሲሆን፣ በዚህ አኳኋን የሚመረጡ የቦርድ አባላት ብዛት ከባንኩ ጠቅላላ የቦርድ መቀመጫ 1/3ኛ መብለጥ የለበትም፣
 14. ከላይ የተጠቀሱት መመዘኛዎች እንደተጠበቁ ሆነው ለዳይሬክተሮች ቦርድ እጩ አባልነት የሚጠቆም ማንኛውም ባለአክሲዮን በብሔራዊ ባንክና በባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ዕምነት የሚጣልበት/ባት፣ ሐቀኛ፣ ጠንቃቃ፣ መልካም ዝናና የተሟላ ስብዕና ያለው/ያላት፣ የባንኩን ዓላማዎችና ራዕይ ለማሳካት በቅንነትና በተነሳሽነት የሚሠራ/የምትሠራ፣የቦርድ አባል ሆኖ ለመሥራት ቁርጠኛ የሆነ/ች መሆን አለበት/ባት፣

ባለአክሲዮኖች ከባንኩ ዋና መ/ቤት  አፍሪካ ጐዳና፣ ፍላሚንጐ አካባቢ፣ ጌት ሐውስ ሕንጻ 5ኛ ፎቅ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት ወይም ከሚቀርባችሁ የባንኩ ቅርንጫፍ ወይም ከባንኩ ድረ-ገጽ www.coopbankoromia.com.et የእጩዎች ጥቆማ ቅጽ በመውሰድ ከግንቦት 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ ከላይ የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ እጩዎችን መጠቆም የምትችሉ መሆኑን አስመራጭ ኮሚቴው  በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ 

 

ባለአክሲዮኖች የሞሉትን ቅጽ በባንኩ ዋና መ/ቤት 5ኛ ፎቅ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ መስጠት ወይም በባንኩ የፖ.ሣ.ቁ. 16936 ፍንፍኔ/አዲስ አበባ ላይ በአደራ ደብዳቤ አድራሻውን ለኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ በማለት ወይም የተሞላውን ቅጽ ስካን በማድረግ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው በባንኩ ኢሜል nominationcommittee@coopbankoromia.com.et  አያይዘው መላክ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡

 

ስልክ ቁጥር  +251 11 558 9769  ወይም +251 929 172973

 

ማሳሰቢያ፤

 1. አስመራጭ ኮሚቴው ከግንቦት 15 ቀን 2010 ዓ.ም. በፊትም ሆነ ከነሐሴ 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ ጥቆማዎችን የማይቀበል መሆኑን ከወዲሁ ያሳስባል፡፡
 2. ጠቋሚው/ዋ ባለአክሲዮን የታደሰ መታወቂያ ካርድ ኮፒ ከጥቆማ ቅጹ ጋር አያይዞ/ዛ ማቅረብ/መላክ ይኖርበታል/ባታል፡፡
 3. በቅጹ ላይ የጠቋሚው/ዋ ባለአክሲዮን ስምና ፊርማ መኖር አለበት፡፡ ጠቋሚው ድርጅት ከሆነ የድርጅቱ ዋና ኃላፊ ፊርማና ሕጋዊ ማኅተም ሊኖረው ይገባል፡፡
 4. ጥቆማው የሚቀርበው በውክልና ከሆነ ሕጋዊ የውክልና ሰነድ ኮፒ ከጥቆማ ማቅረቢያ ቅጹ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
 5. ቅጹ ስርዝና ድልዝ እንዳይኖረው በጥንቃቄ መሞላት ይኖርበታል፡፡

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ

የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ

AGENT BANKING

Deposit
Withdrawal
Payment
Transfer

Icon
Icon
Icon
Icon

COFFEE

CBO finance coffee production, processing, and export.

Icon

TRADE SERVICES

Forex
LC Facility
Import and Export

Icon
Icon
Icon
Image is not available
Image is not available
Image is not available

NEW DEPOSIT PRODUCTS

CBO has launched new deposit products effective at all of its branches.

Image is not available
Image is not available

CARD BANKING

Using CBO card access your account at any ATM in the country.
Make Payment

Icon
Icon

FUEL STATION

Services and products rendered for energy supply activities of the country

Icon
Arrow
Arrow
Slider

Domestic Banking, International Banking, and Electronic Banking.

Customers Deposit Account, Financing, Investment, Kafala Letter of Guarantee Facility, and Trade services.

HelloCash is a Mobile and Agent Banking Service Provided by Cooperative Bank of Oromia.

REMITTANCE AGENTS

swift1.png
swift1.png
Western Union
Western Union
No of Digits: 10 Example: 1234567890 About Western Union The Western Union Company is an American financial services…
dahab.png
dahab.png
expres1.png
expres1.png
kah1.png
kah1.png
money1.png
money1.png
amal1.png
amal1.png
ria1.png
ria1.png
trans1.png
trans1.png
irman1.png
irman1.png
amana1.png
amana1.png
bakal1.png
bakal1.png
juba1.png
juba1.png

RECENT POSTS

Exchange Rate

July 20,2018
TypeBuyingSelling
USD27.3358027.88250
GBP33.8904034.56820
EUR31.6877032.32150

Show More...

© 2018 Coop Bank of Oromia. All Rights Reserved. Designed By HighTech